የክልሉ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ከገቢዎች ባለስልጣን ቢሮ፣ የሀረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት፣ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮና የፕላንና ልማት ኮሚሽን ጋር በገቢ አሰባሰብ ላይ ቅንጅታዊ አሰራርን ለማጠናከርና በገቢ አሰባሰብ ረገድ እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን በተደራጀ አኳኋን ለመቅረፍ የተዘጋጀ የመግባቢያ ሰነድ የተቋማቱ አመራሮች ተፈራርመው ወደ ስራ ተገብቶ የነበረ ሲሆን በዛሬው ዕለት ለሶስተኛ ጊዜ በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ሃላፊ በአቶ መሐመድ ያህያ ሰብሳቢነት አፈጻጸማቸውን በጋራ ገምግመዋል።
በመድረኩም በባለፈው ስብሰባ የተላለፉትን ውሳኔዎች በሚመለከት ከቀጥታ ታክስና ቀጥታ ካልሆነ ታክስ ገቢዎች እንዲሁም ከመሬትና መሬት ነክ ከሚሰበሰቡ ገቢዎችና ሌሎች ውሳኔዎችን አተገባበር ተመልክተዋል።
መንግስት ለሀገር ልማትና እድገት እንዲሁም ለዜጎች ኑሮ መሻሻል ለሚያካሂዳቸው የልማት ስራዎች እና አገልግሎት የሚያስፈልገውን ወጪ ለመሸፈን የክልሉ ኢኮኖሚ ከተለያዩ መስኮች የሚያመነጨውን ገቢ አሟጦ ለመሰብበሰብ ጠንካራ ቅንጅታዊ ስራ እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል። ለዚህም በታክስ አሰባሰብ ስርዓት እና በሌሎች ከመንግስታዊ አገልግሎት የሚሰበሰቡ ገቢዎች ዙሪያ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመቅረፍ የገቢ መጠን እያደገ መሄድ እንዳለበት ተመላክቷል።
ገቢን የሚሰበሰቡ ተቋማት የገቢ አቅማቸውን በአግባቡ ለይተው ጠንካራ ዕቅድ ላይ ተመርኩዘው ተቀናጅተው መስራት እንደሚገባቸው ተጠቅሷል።
ባለድርሻ አካላቱም የገቢ አሰባሰቡን ውጤታማነት ለማረጋገጥ በየጊዜው የዘርፉን አፈፃፀም መገምገም እንዳለባቸው አቅጣጫ ተቀምጧል።
በተጨማሪም የክልሉ መንግስት በ2016 ዓም ከመሬትና መሬት ዘርፍ የሚሰበሰበውን ገቢ ከሌላው ጊዜ በተለየ ሁኔታ ለማሳደግ ያቀደ ሲሆን በመሆኑም በከተማችን የተጀመረውን ዘመናዊ የመሬት መረጃ አያያዝ ስርአትን (ካዳስተር ) በመገንባት የከተማ መሬት አስተዳድር የማሳለጥና የዘርፉን አገልግሎት አሰጣጥ ቀልጣፋ የማድረግ ሂደትን በመደገፍ ከመሬት ዘርፍ የሚገኘውን ገቢ ለማሻሻል እንዲያስችል መሰረታዊ ዋና ዋና ቅድመ ስራዎችን ፤ ፋይል ማደራጀት፣ሬጉላራይዜሽን፣ካርታ ስራ እና ይዞታን የማረጋገጥ ስራን በማበረታቻ ለማሰራት በከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ቢሮ የተዘጋጀ መመሪያን በስፋት በመወያየት በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።
በመጨረሻም በመጨረሻም የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ኃላፊና የኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ መሀመድ ያህያ ለሁሉም አባላት የቀጣይ ስራ አቅጣጫ በመስጠት ውይይቱ ተጠናቋል።