የቢሮ ሃላፊ መልዕክት

የክልሉ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ በአዋጅ ከተሰጡት ተግባርና ኃላፊነት መካከል መንግሥት ከተለያዩ የገቢ ምንጮች የሚሰበስበውን  ሀብት የሚያስተዳደርና እና ወጪውን የሚቆጣጠር ሲሆን ከሴክተር እስከ ወረዳ ድረስ የመንግሥት ሀብት የሚመራባቸዉ የመንግሥት ፋይናንስ አስተዳደር የህግ ማዕቀፎችን በማዘጋጀትና አፈጻጸሙን በመከታተል፣ ለልማት አስፈላጊ የሆነውን በጀት ለመሠረታዊ አገልግሎቶች እንዲውል ጥራትና ፍትሃዊነትን ግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ ያስተገብራል፡፡

መንግስት አገራዊ ኢኮኖሚውን ለማሳደግና የሕዝቡን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል የረጅም፣የመካከለኛና የአጭር ጊዜ ፕሮግራሞች በማዘጋጀትና እና ፕሮጀክቶች በማቀድ በሥራ ላይ የሚያውል ሲሆን አፈጻጸማቸውም የበለጠ ውጤታማ እንዲሆን ቢሮው  ዘመናዊ የመንግስት የሂሳብ አያያዝና የጥሬ ገንዘብ አስተዳደር በመዘርጋት ፣የመንግስትን ሀብት ከብክነት ለመከላከል የሚያስችል ጠንካራ የውስጥ ኦዲት ቁጥጥር በማድረግ ፣ግልጽና ውጤታማ የሆነ የግዥና የንብረት አስተዳደር ስርዓት ከማስፈን፤ የፋይናንስ ስራውን የሚደግፍ ዘመናዊ የመረጃ ስርዓት ከመዘርጋት እና አሰራሩን ከማጠናከር አኳያ በርካታ ስራዎችን መስራት ላይ ነው ።

በተጨማሪም የክልሉ መንግስት ከልማት አጋር ድርጅቶች የሚያገኘውን ሀብት አፈጻጸምን በመከታተል በኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማት ዘርፍ የተሰማሩ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን የክትትልና ድጋፍ ስራ በማከናወን ይገኛል።

በክልላችንን የፋይናንስ ግልጽነትና፣ ተጠያቂነትንና ፍትሃዊነት እንዲሰፍና ለኢኮኖሚ ዕድገት አጋዥ እንዲሆን ሁሉም ባለድርሻ አካል ወጪ ቆጣቢ የሆነ የበጀት ስርአትን በመከተልና ብክነትን በመቀነስ የሚመደበው በጀት ለታለመለት አላማ እንዲውል በማድረግ  የበኩሉን  አስተዋፅኦ እንዲያበረክት መልዕክቴን አስተላልፋለሁ።

አመሰግናለሁ!!

አቶ መሐመድ ያህያ ባሻ

የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ኃላፊ