መንግስት በየዓመቱ የሚመድበው በጀት የአገሪቱን የዕድገት ዓላማ ለማሳካትና ድህነትን ለመቀነስ ብሎም ለማስወገድ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ መንግስት አገራዊ ኢኮኖሚውን ለማሳደግና የሕዝቡን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል ካፒታል ፕሮጀክቶችን በማቀድ በሥራ ላይ የሚያውል ሲሆን አፈጻጸማቸውም የበለጠ ውጤታማ የሚሆነው፣ ለፕሮጀክቶቹ ማስፈፀሚያ የሚያስፈልጉ የፋይናንስ የሰው ሃይል በተቀናጀ ዕቅድ ሲመራ ነው፡፡
ዘንድሮ በክልላችን ከግንቦት 27/2016 ጀምሮ ለአንድ ወር ዓለም አቀፍ የሀረር ቀን እንደሚከበር ይታወቃል። በዚህም መሰረት በዓሉ በክልላችን መከበሩ በአገር ውስጥና በውጭ አገራት የሚኖሩ ሀረሪዎች ፤ የሀረር ተወላጆችና ወዳጆች እንዲሁም አጎራባች ክልሎች ፤ እህትማማች ከተሞችና ህዝቦች የሚሰባሰቡበት በመሆኑ ፍቅርና መቻቻልን የሚያጠናክር ብሎም መልካም ገጽታ ፤ የኢንቨስትመንት ፍሰትና የቱሪዝም ክፍለ ኦኮኖሚን የሚያጎለብት መልካም አጋጣሚ ይፈጥራል ተብሎ ይታመናል፡፡
በዓሉ በሚፈልገውና በሚጠበቀው ደረጃ ለማሳካት እንዲያስችልና የክልሉን መልካም ገጽታ ለመገንባት የሚያስችሉ ተግባራት አካል የሆኑ የካፒታል ፕሮጅክቶች እቅድን በክልሉ የተቋቋመው የካፒታል ፕሮጅክቶች ክትትል ኮሚቴ የእቅዱን መርሃ ግብር ገምግሟል።
ኮሚቴው በገምገማው የካፒታል ፕሮጀክቶች ጊዜ ገደባቸውን ጠብቀው መሄድ እንዳለበትና ፈፃሚ አካላትም የስራውን አላማ ከግብ እንዲደርስ የተቀናጀና የተደራጀ ርብርብ ማድረግ እንዳለበቸውም ጠቁመዋል ።
ዓለም አቀፍ የሀረር ቀን እቅድ መሳካቱ በርካታ ፋይዳዎች ያሉት እንደመሆኑ የሚመለከታቸው አካላት /ሴክተሮች/ የዚህ በዓል አከባበር ሁለንተናዊ ፋይዳ በጥልቀት ግንዛቤ ውስጥ ማስገባት ከግንቦት 30 በፊት የካፒታል ፕሮጀክቶች መጠናቀቅ እንዳለባቸውና ለተፈፃሚነት ሁሉም የስራው አካላት ልዩ ትኩረት መስጠት እንዳለባቸው የካፒታል ፕሮጀክቶች ክትትል ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ መሐመድ ያህያ ስራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።