የሀረሪ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ለሴክተርና ወረዳ የሂሳብ ባለሙያዎች 2ኛ ዙር የIBEX ሶፍትዌር ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡
በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ በቻናል አንድ ፕሮግራም በየአመቱ ቢሮው በተለያዩ ዘርፎች ስልጠናዎችን እየሰጠ ይገኛል። ወደፊትም ይህ ቀጣይነት ያለው ተግባር እንደሆነና የስልጠናው ዋና አላማ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣውን የመንግስት ልማት ማስፈጸሚያ በጀት በቴክኖሎጂ የተደገፈና ውጤት ሊያመጣ በሚችል ሁኔታ ለመፈጸም የመንግስት ሂሳብ አያያዝና የበጀት አስተዳደር ስርዓቱን በIBEX ሶፍትዌር የታገዘና አሰራሩን ቀልጣፋ፣ ዘመናዊና ቀላል ለማድረግ ታስቦ እንደሆነ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ምክትል ኃላፊ የሆኑት አቶ አብዱልባሲጥ አቡበከር ገልጸዋል ፡፡
አያይዘውም የፕሮግራሙ ሂሳብ እና መደበኛ ሂሳብ በዘመናዊ ቴክኖሎጅ በሆነው በIBEX System በመጠቀም ፈጣንና ጥራት ያለው የሂሳብ አያያዝ እንዲኖርና ወቅቱን የጠበቀ የሂሳብ ሪፖርት ለማዘጋጀትም እንዲጠቅም ታስቦ የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑን ገልፀዋል፡፡የበጀት አስተዳደር እና ቁጥጥር ስርዓቱን ውጤታማ ለማድረግ እዚህ ላይ የበለጠ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ከስልጠናው ተሳታፊዎች እንደሚጠበቅ አሳስበዋል፡፡
የIBEX ሶፍትዌር ቴክኖሎጂውን በቀላሉ ተፈጻሚ ለማድረግ በዘርፉ ለተስማሩ ባለሙያዎች ቢሮው የተለያዩ ስልጠናዎችን በተለያዬ ጊዜያት ሲሰጥ የቆየ ቢሆንም ሰልጥኖ ወጥቶ ወደተግባር በመግባት በሰለጠኑት ልክ አውቆና ተረድቶ መፈጸም ላይ ያልዉን ከፍትት በመቅረፍ በዘርፉ ውጤታማ ስራ መስራት አንደሚገባ አሳስበዋል ፡፡ከዚህ ስልጠና መልስም በሰለጠኑበት አግባብ የተግባር ላይ ልምምድ በማድረግ እና ለሌሎች ባለሙያዎች ጭምር ማሳወቅ እንዳለባቸው አቶ ይማጅ አህመድ የኢንፎርሜሽ ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአንክሮ ገልጸዋል፡