በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ የአጠቃላይ የትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም ከተለያዩ ሴክተርና ወረዳዎች ለተውጣጡ የበጀት ዝግጅትና አስተዳደር ባለሙያዎች የተቀናጀ የበጀት አስተዳደር /IBEX/ ስልጠና በዙር እየሰጠ ይገኛል፡፡
የተቀናጀ የቀጀትና ወጪ ስርዓት(IBEX) በአገር አቀፍ ደረጃ የመንግስት ሂሳብ የሚሰራበት የመንግስትን ሂሳብ አያያዝና የበጀት ስርዓቱን በአንድ ላይ በማጣመር ቀልጣፋ በሆነ መንገድ ስራዎችን ለማከናወን የሚያስችል ሶፍትዌር ነው። የተቀናጀ የበጀትና የወጭ መረጃ ስርዓት(Integrated Budget and Expenditure System–IBEX ) የመንግስት የፋይናንስ አስተዳደርን ለመደገፍና ለማቀላጠፍ የተዘረጋ ስርዓት መሆኑ ይታወቃል፡፡
የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ በየደረጃው ያሉ ባለሙያዎች በዘርፋ በቂ እውቀት ይዘው ተግባሩን ውጤታማ ማድረግ እንዲችሉ ተከታታይ ስልጠናዎችን እየሰጠ ይገኛል