በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ የዋና ኦዲት ዳይሬክቶሬት ከክልሉ ሴክተር ተቋማት ለተውጣጡ የውስጥ ኦዲት ባለሙያዎች የፋይናንሻልና ኦዲት ስልጠና መስጠት ጀምሯል ፡፡
የውስጥ ኦዲት ባለሙያዎች በአጠቃላይ የውስጥ ኦዲት አሰራር ዙሪያ በቂ ክህሎትና ግንዛቤ ኖራቸው የአዲት ባህሪያት ማለትም ሚሰጢር ጠባቂነት፣ገለልተኝነት፣ ተአማኒነትና ሙያዊ ብቃትን መላበስ እንደሚያስፈልግም ተመላክቷል።
ጠንካራ የውስጥ ቁጥጥር ስርዓት በመዘርጋትና የተቋሙ ኃላፊ ብቁ አማካሪ ሆኖ በመገኘት ስህተቶች ከመፈጸማችው በፊትና ምናልባትም ስህተቶች ከተፈጸሙ በኋላ ተገቢ ማስተካከያና እርምት እንዲወሰድ በማድረግ በኩል የሚጠበቅባቸውን ድረሻና ኃላፊነት እንዲወጡ በማሰብ ስልጠናው እንደተዘጋጀ በቢሮው የ ዋና ኦዲት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ኻሊድ አብዱልከሪም ገልፀዋል።
የውስጥ ኦዲተሩ የተቋማቸውን እቅድና ሪፖርት በወቅቱ መላክ እንዲሁም የዘመኑ እና የውዝፍ ኦዲት መረጃ ማጥራትና ለተቋሙ አቅርቦ ግኝት ማስመለስ ስራ በአግባቡ ሊሰራ እንደሚገባ ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡