የዕለቱን መርሐ ግብር በማስመልከት በንግግር የከፈቱት የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ሃላፊ አቶ መሐመድ ያህያ የውስጠ ፓርቲ ስራችን ለማጎልበት አደረጃጀቶችን የማጠናከር ስራ መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል።
ብልፅግና ፓርቲ ያለፉ ህፀፆችን በማረም፣ በጎዎችን በማዳበር ኢትዮጵያን የሚመስል ብልፅግና በማረጋገጥ እውነተኛ ዴሞክራሲን ለመትከል ግብ ይዞ በመስራት ላይ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
የጠንካራ ፓርቲ ግንባታ ተግባራዊ ለማድረግ የአላማ ፅናት ሊኖረን ይገባል በማለት አሁን ያለውን ቅንጅትና ትብብር መንፈስ ይበልጥ በማጠናከር ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ ልንታትር ይገባል ሲሉ አፅኖት ሰጥተዋል።
በመድረኩ ላይ የጠንካራ ፓርቲ ግንባታ አቅጣጫ፣ የጠንካራ ፖለቲካ ፓርቲዎች መሠረታዊ መመዘኛዎች፣ ጠንካራ ተቋማዊ አቅም መፍጠር፣ የፓርቲ ቀጣይ ተልዕኮና ተግባራት በሚሉ ዋና ዋና ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በቢሮው ም/ሃላፊ አቶ ኻሊድ አብዲ ሰነድ ቀርቦ ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጓል ።
ቢሮ ሃላፊው በማጠቃለያ ሃሳባቸው እንደገለፁት ብልፅግና የሃሳብ ልዕልና ያለው ፓርቲ በመሆኑ የብልፅግና ዓላማና ግቦችን መሰረት በማድረግ አቅማችን እያጎለበትንና እራሳችንን እያበቃን ፊትለፊት የሚገጥሙንን ተግዳሮቶችን እየተጋፈጥን ከፋይናንስ ሴክተር አንፃር ህዝቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማት ተግባራት መፈፀም ይኖርብናል ብለዋል።
በመጨረሻም በተሰጠው ስልጠና ነክ ግንዛቤ ማስጨበጫ ከመድረክም ሃሳቡን በማዳበር ውይይቱ ተቋጭቷል።