በመዘናጋት በሀገሪቱ እያንሰራራ የመጣውን የኤች አይቪ/ኤድስ ስርጭት ለመግታት ሁሉም ባለድርሻ አካላት ርብርብ እንዲያደርጉ ተጠየቀ።
የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ከሀረሪ ክልል ኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ለቢሮው ሰራተኞችና ቤተሰቦቻ
ቸው በኤች አይ ቪ ዙርያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል ።
በመድረኩ ላይ የተገኙት በሀረሪ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ም/ቢሮ ሃላፊ የሆኑት አቶ ኻሊድ አብዲ እንዳሉት በአሁኑ ወቅት ለኤች አይ ቪ ኤድስ የሚሰጠው ትኩረት በማነሱ ምክንያት ስርጭቱ እንዲጨምር አድርጓል ብለዋል።
ስለሆነም ከኤችአይቪ ጋር በተያያዘ እየታዩ የሚገኙ መዘናጋቶች መቅረፍ ይገባል ብለዋል።
የሀገሪቱን ብልፅግና ለማረጋገጥ ጤናው የተጠበቀና አምራች ዜጋን መፍጠር አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል።
እንደ ሃገርም ሆነ እንደ ክልል አሁን ላይ ያለው የኤች አይ ቪ ኤድስ የስርጭት ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እና አሳሳቢ ደረጃ ላይ እየደረሰ መሆኑን ሁሉም የቢሮው ሠራተኞች ግንዛቤ እንዲኖራቸው የተደረገ ሲሆን በዘርፉ የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት ሰጥተው መስራት እንደሚገባቸው የቢሮው ሠራተኞች በመግለጽ እኛም የበኩላችንን ድርሻ በመወጣት የበሽታውን ስርጭት ለመቅረፍ ጠንክረን መስራት ይገባናል ብለዋል፡