የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ በመሰረታዊ የበጀት አዘገጃጀትና አመዳደብ ዙሪያ ለሴክተርና ወረዳ የየፋይናንስ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች ስልጠና ሰጠ፡፡
የስልጠናው ዋና አላማ በበጀት አስተዳደር ቁጥጥር አጠቃቀምና በጀት ዝውውር ዙሪያ የሚስተዋሉ ችግሮችን መቅረፍ የሚያስችል ክህሎት በማዳበር በዘርፉ የሚሰሩ አመራሮች እና ባለሙያዎች በእውቀት ላይ ተመስርተው የበጀት አስተዳደርና ቁጥጥር ስርዓቱን እንዲመሩ ከማድረግ በተጨማሪም በክልሉ ወጥ የሆነ የጀት አስተዳደር እና ቁጥጥር ስርዓት በመዘርጋት የተመደበውን በጀት በእቅድ ላይ ተመስርቶ ለታለመለት ዓላማ እንዲውል በማድረግ ውጤት ለማምጣት ታስቦ እንደሆነ በስልጠናው ተገልጿል፡፡
የበጀት አስተዳደር እና ቁጥጥር ስርዓቱን ውጤታማ ለማድረግየበለጠ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚያስፈልግም ተገልጿል ፡፡ የዘርፉ ባለሙያዎችና ሀላፊዎችም በስልጠናው ያገኙትን ዕውቀት ወደ ተግባር በማውረድ ስራዎቸችውን መፈጻም እንዳለባቸው አሰልጣኛ አሳስበዋል፡፡