የበጀት ስራ በህግና በጊዜ ማዕቀፎች የሚመራ፣ ሰፊ የዝግጅት ስራና ትኩረት የሚያስፈልገዉ የመንግስት ልማት ዕቅድ ማስፈፀሚያ መሳሪያ መሆኑ ይታወቃል ። በክልላችን በየበጀት ዓመቱ ለመንግስት ስራዎች ማስፈፀሚያ በጀት ሲታወጅ የበጀት አስተዳደር ስርዓት በተለያዩ የአስተዳደር እርከኖች እየተዘጋጀ፣ እየፀደቀና እየተፈቀደ ስራ ላይ እንደሚዉል የሚታወቅ ነዉ፡፡
በዚህ መነሻ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ለሚመለከታቸው አካላት የበጀት ዝግጅትና አስተዳደር ላይ ስልጠና ሰጥቷል፡፡ የስልጠናው ዋና አላማ በበጀት አስተዳደር ቁጥጥር አጠቃቀምና በጀት ዝውውር ዙሪያ የሚስተዋሉ ችግሮችን መቅረፍ የሚያስችል ክህሎት በማዳበር በዘርፉ የሚሰሩ አመራሮች እና ባለሙያዎች በእውቀት ላይ ተመስርተው የበጀት አስተዳደርና ቁጥጥር ስርዓቱን እንዲመሩ ከማድረግ በተጨማሪም በክልሉ ወጥ የሆነ የጀት አስተዳደር እና ቁጥጥር ስርዓት በመዘርጋት የተመደበውን በጀት በእቅድ ላይ ተመስርቶ ለታለመለት ዓላማ እንዲውል በማድረግ ውጤት ለማምጣት ታስቦ እንደሆነ በስልጠናው ተገልጿል፡፡
የበጀት ጥያቄ በወቅቱና በጥራት አዘጋጅቶ አለማቅረብ፣ የሂሳብ አንቅስቃሴ በአይቤክስ አለመመዝገብ፣ ተሰብሳቢና ተከፋይ ሂሳቦች ሁሌም ችግርና የመሳሰሉት ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እንደነበሩ በውይይቱ ተነስተዋል፡፡
በጀት ድልድልና አስተዳደር ላይ የታዩ ዋና ዋና ችግሮችን በመፍታት በቀጣይ የተሻለ የበጀት አስተዳደር መፍጠር እንደሆነም ተናግረዋል፡፡
የበጀት አስተዳደር እና ቁጥጥር ስርዓቱን ውጤታማ ለማድረግየበለጠ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ከስልጠናው ተሳታፊዎች እንደሚጠበቅ ተገልጿል ፡፡ከዚህ ስልጠና መልስ የዘርፉ ባለሙያዎችና አመመራሮች በስልጠናው ያገኙትን ወደ ተግባር በማውረድ ስራዎቸችውን መፈጻም እንዳለባቸው አሰልጣኞቹ አሳስበዋል፡፡