የስራ ክፍሎች

 • የመንግስት በጀት ያዘጋጃል፣ የበጀቱን አፈጻጸም ያስተዳደራል፣ ይገመግማል፤ ይቆጣጥራል፤
 • በበጀት የተደገፉ የመንግስት ፕሮጀክቶች የአፈጻጸም አግባብነትን በመገምገም የክፍያ ስርዓት ተፈጻሚ እንዲሆን ያደርጋል፤
 • ወቅቱን ጠብቆ ለክልል ሴክተር መ/ቤቶች የበጀት ጥሪ ያስተላልፋል፤ የባለበጀት መ/ቤቶችን የበጀት ስሚ ያደርጋል፤
 • የቀረበውን የበጀት ጥያቄ በመመርመር በበጀት ስሚ የተሰጡትን አስተያየቶች ከሀብት ጋር በማጣጣም በበጀት ይደግፋል፤ የተደገፈውን በጀት በማጠቃለል፤ ረቂቅ የበጀት እቅድ ለሚመለከተው አካል ለአስተያየት ያቀርባል፤
 • የተሰጠውን ግብአት በማካተት ረቂቅ የበጀት እቅዱን በቢሮው በኩል ለክልሉ መንግስት ያቀርባል፤
 • የክልል ማዕከልና የአሰተዳደር ዕርከን ሴክተር መ/ቤቶች የተደለደለው በጀት አፈጻጸሙን በመከታተልና በመገምገም ለሚመለከተው አካል ርፖርቱን ያቀረባል፤
 • ለአስተዳደር እርከኖችና ለክልል መ/ቤቶች ተደልድሎ በክልሉ መንግስት የፀደቀውን የበጀት አዋጅ ያሳውቃል፤
 • ተጨማሪ የበጀት ጥያቄ በማደራጀት የበጀት ድጋፍ ያጠቃልላል፤ ሲፀድቅም ያሳውቃል፤
 •  የበጀት አዘገጃጀትና አቀራረብ መመሪያ ያዘጋጃል፤
 • በቀመር ተደልድሎ በክልሉ መንግስት የበጀት አዋጅ የፀደቀውን የአስተዳደር እርከኖች ጥቅል በጀት (Block Grant) እና የባለ በጀት መ/ቤቶች ዓመታዊ በጀት በደብዳቤ ያሳውቃል፤
 •  የፀደቀ በጀት በባለ በጀት መ/ቤት፣ በሥራ ክፍልና በወጪ መደብ ትክክለኛነታቸውን በማረጋገጥ ያፀድቃል፤ ያሳውቃል፤
 • በአይቤክስ ሲስተም ላይ በጀትን ለማደራጀት የበጀት ዓመት /Create Budget Year/ ይፈጥራል፤ የበጀት ዓመቱን የበጀት መዋቅር ያስተካክላል /Edit Budget Structure
 • ዓመታዊ በጀት በሥራ ክፍልና በበጀት ኮድ በመዘርዘር ያዘጋጃል፤ ያጠቃልላል፤
 • አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ጥናት በማድረግ የበጀት መዋቅር ማሻሻያ ሀሳብ ለዘርፉ ያቀርባል፤
 • የክልል ባለበጀት መ/ቤቶችን የድርጊት መርሃ ግብር (Action Plan) ያጠቃልላል፤
 • የወጪ ጥያቄዎች በዕቅድ መከናወናቸውን ይቆጣጠራል፤
 •  የጥሬ ገንዘብ ፍላጎት መርሃ ግብር (Cash Request) በማዘጋጀት ያስተላልፋል፤ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ይከልሳል፤
 • የክልሉን የገቢ በጀት መረጃ በፋይናንስ ምንጭ (የፌደራል ድጎማ፣ የውስጥ ገቢ፣ ብድርና እርዳታ) በዝርዝር ሴክቶራል በሆነ መልክ በአይቤክ ሲስተም ያስተዳድራል፤
 • ከብድር እና እርዳታ የሚገኝ በጀት በትክለኛው የአበዳሪ ወይም ረጂ ድርጅት ኮድ የተመዘገበ መሆኑን ያረጋግጣል፤
 •  ዓመታዊ የካፒታልና መደበኛ በጀት በአይቤክስ ሲስተም ያፀድቃል/Approve the Budget/
  • ከወረዳዎችና ና የክልል ሴክተር መ/ቤቶች የሚመጣ የፀደቀ በጀት በትክክለኛው የሥራ ክፍልና የወጪ መደብ የተመዘገበ መሆኑን መርምሮ ያረጋግጣል፤
 •  አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የፀደቀ በጀት ወደኋላ በመመለስ /Demote the Approved Budget ያስተካክላል፤
 •  የተጨማሪ በጀትና የበጀት ዝውውር መረጃ የተስተካከለ በጀቶችን መረጃ በዝርዝር በካፒታልና በመደበኛ በጀት ትክክለኛነታቸውን መርምሮ ይመዘግባል፣ ያረጋግጣል፤ ያጠናቅራል፤
 •  የክልሉን ዓመታዊ በጀት መረጃ በዘርፍ፣ በሴክተርና በሥራ ክፍልና በወጪ መደብ በየአስተዳደር እርከኑ በፋይናንስ ምንጭ ያጠቃልላል፤
 •  ከበጀት የወጣውንና የቀረውን እንዲሁም የተስተካከለውን በጀት ያገናዝባል፤
 • የበጀት መረጃ ስርዓት ያስተዳድራል ለውሳኔ በሚመች መልኩ አደራጅቶ ተደራሽ ያደርጋል
 • የዓመታዊ በጀት መረጃን ለበጀት መፅሀፍና በጀት አዋጅ ለማሳተም በሚያመች ሁኔታ ያጠቃልላል፤ እንዲታተም በማድረግ ያሰራጫል
 •  የባለሙያዎች የአቅም ክፍተት በመለየት አቅማቸው የሚጎለብትበትን ሁኔታ ያመቻቻል አፈጻጸሙን ይከታተላል
 • በበጀትና ፋይናንስ ላይ በተዘጋጁ አዳዲስ የአሠራር ሥርዓቶች፣ ማኑዋሎችና ሶፍትዌሮች ላይ ስልጠናና ሙያዊ ድጋፍ ይሰጣል፤
 •  የሥራ ክፍሉን የሚያቀላጥፉና ውጤታማ የሚያደርጉ የአሰራር ዘዴዎችን ይቀይሳል ተግባራዊ እንዲሆኑ ያደርጋል
 •  የዳይሬክቶሬቱን ዓመታዊ፣ የሩብ ዓመት፣ የግማሽ ዓመት፣ የዘጠኝ ዓመት ዕቅድና የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቶችን ለቅርብ ኃላፊና ለቢሮ በተቀመጠዉ የጊዜ ገደብ ያቀርባል፣
 • ዳይሬክቶሬቱን በሚመለከቱ በተለያዩ ስብሰባዎች፣ሴሚናሮች ላይ በመገኘት የልምድ ልዉዉጦችንና ግንዛቤ በመቀመር በዳይሬክቶሬት ሥር የሚገኙ ባለሙያዎችን ዉጤታማ የሆነ ሥራ እንዲያከናወኑ ማድረግ፣የተገልጋዮችን እርካታ ደሰሳ ጥናት እንዲካሄድ በማድረግ የዳይሬክቶሬቱን አገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓት የሚሻሻልበት ሁኔታ ይቀይሳል፣
 • በዳይሬክቶሬቱ የሰዉ ኃይል በመዋቅሩ መሠረት እንዲሟላ ያደርጋል፣
 • በዳይሬክቴሩ የሚያስፈልጉ የሥራ ቁሳቁሶች እንዲሟላ ያደርጋል፣
 • ዳይሬክቶሬቱን ዓመታዊ፣ የሩብ ዓመት፣ የግማሽ ዓመት፣ የዘጠኝ ዓመት ዕቅድና የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቶችን ለቅርብ ኃላፊና ለቢሮ በተቀመጠዉ የጊዜ ገደብ ያቀርባል፣
 • በክልሉ ምክር ቤት የፀደቀዉን ዓመታዊ በጀት መነሻ በማድረግ በመደበኛና በካፒታል፣ በደመወዝና በሥራ ማስኬጃ በመለየት በክልል ባለበጀት መሥሪያ ቤቶችና በክልለ ተቋማት ሥር በሚገኙ የስራ ክፍሎች፣ በዞኖች፣ በልዩ ወረዳዎች፣ በወረዳዎች እና በከተማ አስተዳደር ስም የበጀት መረጃ ለይቶ በመያዝ ይቆጣጠራል፣
 • ለዓመቱ የተፈቀደዉን በጀት መነሻ በማድረግ ከፌዴራል የሚገኝ ድጎማ ገቢ፣ ከክልል ባለበጀት መሥሪያ ቤቶች፣ ከከልል ተቋማት፣ ከዞኖች፣ ከልዩ ወረዳ፣ ከወረዳ እና ከከተማ አስተዳደር ለመሰብሳብ በዕቅድ የተያዘዉን መረጃ አደራጅቶ በመያዝ አፈፃፀሙን ይከታተላል፣
 • ከሁሉም የአስተዳደር እርከኖች የጥሬ ገንዘብ ፍላጎት በመሰብሰብ ዓመታዊ የጥሬ ገንዘብ ፍላጎት መርሃ ግብር በማዘጋጀት ለፌዴራል ገንዘብ ሚኒስቴር ያቀርባል፣
 • ከክልሉ ለፌዴራል ገንዘብ ሚኒስቴር በቀረበዉ ጥሬ ገንዘብ ፍላጎት መርሃ ግብር መሠረት የድጎማ በጀት ወይም ገቢ በወቅቱ መላኩን ይከታተላል፣
 • የክልል ቢሮዎች የሚያቀርቡትን የክፍያ ጥያቄ በመቀበል ከተፈቀደላቸዉ በጀትና የጥሬ ገንዘብ ፍላጎት መርሃ ግብር መሠረት የቀረበ መሆኑን በማጣራት የባንክ ጣሪያ ይመሰርታል፣
 • የክልል ባለበጀት መሥሪያ ቤቶች የተሰጣቸዉን የባንክ ጣሪያ መነሻ በማድረግ ከፍያ መፈፀማቸዉንና ከማዕካለዊ ግምጃ ቤት በጥሬ ገንዘብ መተካቱን ያረጋግጣል፣
 • ከሁሉም አስተዳደር እርከኖች ተንከበላይ የ3 ወራት የጥሬ ገንዘብ ፍላጎት መርሃ ግብር ተዘጋጅቶ እንዲቀርብ በማድረግ በቀረበዉ መርሃ ግብር መሠረት ይፈፅማል፣
 • በየወሩ ለወረዳዎች የቀረበዉን የጥሬ ገንዘብ ፍላጎት መርሃ ግብርና የተፈቀደላቸዉን በጀት መነሻ በማድረግ የባንክ ማዛዣ ደብደቤ በማዘጋጀት የጥሬ ገንዘብ ዝዉዉር ይፈጽማል፣
 • ለክልል ባለበጀት መሥሪያ ቤቶች፣ ለክልል ተቋማት የደመወዝ ገንዘብ ሲተላለፍ የሲቪል ሠራተኞችና የሚሊተሪ የሠራተኞችና የመንግሥት የጡረታ መዋጮ ድርሻ ከሚተላለፈዉ ገንዘብ ቀንሶ በማስቀራት በየወሩ ለብሔራዊ ባንክ ያስተላልፋል፣
 • የመንግሥት ገንዘብ በታለመለት ዓላማ ላይ ዉጤታማ በሆነ መንገድ እንዲዉል ለማድረግ ዘመናዊ የመንግሥት የጥሬ ገንዘብ አስተዳደር ሥርዓት በየደረጃዉ ወጥነት ባለዉ መንገድ እንዲዘረጋ ያደርጋል፣
 • በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በሳጥን የሚያዝ የጥሬ ገንዘብ ጣሪያ በመወሰን በዉሳኔዉ መሠረት እንዲተገበር ያደርጋል፣
 • የክልሉ የተጠቃለለ ፈንድ አካዉንት ሂሳብ መቆጣጠርና ማስተዳደር፣
 • የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችን የባንክ ሂሳቦችን መክፈት፣ መቆጣጠር፣ ማስተዳደር እና የማይቀሰቀሱ የባንክ ሂሳቦችን ይዘጋል፣
 • በአመታዊና በተንከበላይ የ3 ወር የጥሬ ገንዘብ ፋላጎት መርሃ ግብር መሠረት ይገኛል ተብሎ በዕቅድ የተያዘ ገንዘብ፣ የተከፈለዉ እና ከወጪ ቀሪ የገንዘብ ሚዛን የሚያሳይ የገቢና የወጪ መግለጫ አዘጋጅቶ በመገምገም የአፈፃፀሙ ሪፖርቱን ለሚመለከታቸዉ አካላት ያቀርባል፣
 • በክልል ባለበጀት መሥሪያ ቤቶች ዜሮ ሚዛን የክፍያ ሥርዓትን በማሻሻል ዘመናዊ የጥሬ ገንዘብ ፍሰት ሥርዓት ይዘረጋል፣
 • በዞንና በወረዳ የሚተገበረዉን አንድ የፋይናንስ የጋራ አገልግሎት(ፑል) ክፍያ ሥርዓት በመገምገም የሚታዩ ክፍተቶችን በማረም ወቅቱ የሚፈልገዉን ቴክኖሎጂ በመጠቀም የአሰራር ሥርዓቱን ዘመናዊ እንዲሆን ያደርጋል፣
 • ከመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የፈሰስ ሂሳቦች በወቅቱ ወደ ማዕከላዊ ግምጃ ቤት ገቢ እንዲሆን ያደርጋል፣
 • በክፍያ አፈጻጸም ላይ ክፍተት ያለባቸዉን የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችን በመለየት የድጋፍና የክትትል ሥራዎችን በማከናወን ግብረ መልስ ይሰጣል፣
 • የአቅም ግንባታ ክፍተቶችን በመለየት በክፍያ አፈጻጸም ዙሪያ የሚታዩ የአፈጻጸም ችግሮችን በመለየት የሥልጠና ሰነድ አዘጋጅቶ ሥልጠና ይሰጣል፣
 • በቢሮ በሚዘጋጁ የዉይይት መድረኮች ላይ በመገኘት በክፍያና በጥሬ ገንዘብ አስተዳደር ዙሪያ በሚነሳ ጥያቄዎች ላይ ማብራሪያ ይሰጣል፣
 • የጥሬ ገንዘብ አስተዳደርና የክፍያ አሰራር ሥርዓትን በተመለከተ የሚፈለጉ መረጃዎችን አደራጅቶ ለገንዘብ ሚኒስቴርና ለሌሎችም አካላት ያቀርባል፣
 • በሁሉም አስተዳደር እርከን በጥሬ ገንዘብ አስተዳደርና አጠቃቀም ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን በጥናት በመለየት ችግሮቹን በዘላቂነት እንዲፈታ ያደርጋል፣
 • ከዉስጥ ኦዲት ዳይሬክቶሬት ጋር በማቀናጀት አለአግባብ የተከፈሉ ክፍያዎች ተመላሽ ሆነዉ ወደ ማዕከላዊ ግምጃ ቤት ገቢ እንዲሆን ያደርጋል፣
 • የመንግሥት ፋይናንስ አስተዳደር አዋጆች፣ ደንቦች፣ መመሪያዎች እና የአሰራር ማንዋሎች ሲዘጋጁ የጥሬ ገንዘብ አስተዳደርና የክፍያ አሰራር ሥርዓትን በተመለከተ አሰራር ሥርዓትን ዉጤታማ ሊያደርጉ የሚችሉ ሀሳቦችን ያቀርባል፣
 • የመንግሥት ገቢ የሚሰበሰብባቸዉ የገቢ ደረሰኞች በጥንቃቄ እንዲጠበቁ ክትትል ያደርጋል፣
 •  የመንግሥት ገንዘብ ክፍያ የሚፈጸምባቸዉ የሂሳብ ሰነዶችና ቼኮች በአግባቡ እንዲጠበቁ ያደርጋል፣
 • ክፍያ የተፈጸመባቸዉ የክፍያ ሰነዶች በወቅቱ በተቀናጀ በፋይናንስ አስተዳደር መረጃ ቋት(IBEX) እንዲመዘገቡ ለሂሳብና ሪፖርት ማጠቃለያ ዳይሬክቶሬት በየዕለቱ ያስተላልፋል፣
 • በዳይሬክቶሬቱ የሰዉ ኃይል በመዋቅሩ መሠረት እንዲሟላ ያደርጋል፣
 • በዳይሬክቴሩ የሚያስፈልጉ የሥራ ቁሳቁሶች እንዲሟላ ያደርጋል፣
 • በቢሮ የዳይሬክቶሬቱ መዋቅር ሲዘጋጅ አስፈላጊዉን ግብዓቶችን በማቅረብ አብሮ ያዘጋጃል
 • የግዥና ንብረት አስተዳደር ኦዲት ተግባራት፣የግዥና ንብረት አስተዳደር ስርዓትን፤ በበላይነት ይመራል፣  ፤ ይቆጣጠራል፤ የአሰራር መመሪያዎችና ማንዋሎች እንዲዘጋጁ ያደርጋል ሲጸድቅም ስራ ላይ እንዲውል ያደርጋል፤
 • የኦዲት ሪፖርቱን መሰረት በማድረግ የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር የኦዲት ተግባራት የሚሻሻሉበትን  ሃሳቦችን ያቀርባል ሲፈቀድም፣ ተግባራዊ ያደርጋል
 • በአገር አቀፍ እና በአለም አቀፍ በሚወጡ ጨረታዎችና የዋጋ ማቅረቢያዎች ላይ በዕቃ፣ በግንባታ፣ በምክር አገልግሎት እና በንብረት አወጋገድ የሚታዩ የአፈፃፀም ጉድለቶች ላይ በሚቀርቡ አቤቱታዎች፤ጥፋተኝነት ሪፖርቶች፤ከሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን እና ከሌሎች ከሚመለከታቸው ተቋማት ተጣርተው አስተያየት እንዲሰጣቸው የተጠየቁትን በማጣራት የውሳኔ ሃሳብ ለማዘጋጀት የሚያስፈልጉ የተሰበሰቡ መረጃዎችን  ለውሳኔ አስተያየት ያደራጃል፣ዉሰኔ እንድ ሰጥ ያመቻቻል.

ለመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር የሚረዱ ፖሊሲዎች፣ አዋጅ ፣መመሪያዎች እና ማንዋሎች እንዲዘጋጁ ፣እንዲጸድቁና እንዲተገበሩ ያደርጋል፣

የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ስራዎች በቅንጅት የሚሰሩበትን ሁኔታ ያመቻቻል፣

 • የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኦዲት አሰራር እና አቤቱታዎችን ለማጣራት የሚረዱ   ፣መመሪያዎች እና ማንዋሎች እንዲዘጋጁ ያስተባብራል፣እንዲጸድቁና እንዲተገበሩ ያደርጋል፣
 • የመንግስት ግዥ ስርዓት፡ ንብረት አስተዳደር እና ግዥና ንብረት አስተዳደር የኦዲት  ስራዎች በቅንጅት የሚሰሩበትን ሁኔታ ያመቻቻል፣
 • በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ዙሪያ በአገር ዓቀፍ ደረጃ እና በክልል ደረጃ ምርጥ ተሞክሮዎች እንዲሰበሰቡ፣እንዲቀመሩ እና ተስማሚ የሆኑትን መርጦ እንዲተገበሩ ያደርጋል፣
 • ከመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር፤ ኦዲት አሰራር ፤ግዥና ንብረት አወጋገድ ጋር በተያያዘ ከሚሰሩ አጋር አካላት ጋር የትብብር ፎረም ያዘጋጃል፣የጥናት ጽሁፎችን ያቀርባል፣
 • የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ስራዎች በአግባቡ እንዲከናወኑ፣ወቅታዊ እና ተከታታይ የአፈጻጸም ግምገማዎች እንዲካሄዱና የአፈጻጸም ሪፖርቶች እንዲዘጋጁ ያደርጋል፣
 • የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ማነቆዎችን በመፍታት የዘርፉን ልማት የሚያግዙና ተወዳዳሪ የሚያደርጉ የቴክኖሎጂና የስራ አመራር ስርዓት በመዘርጋት ውጤታማነታቸውን ይከታተላል፣ያረጋግጣል፣
 • የመንግስት ግዥና ንብራት አስተዳደር መረጃ አያያዝና አጠቃቀም በዘመናዊ መልኩ መደራጀቱን ያረጋግጣል፣
 • ኢ-ፕሮኩርመንትን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል የአሰራር ስርዓት ይዘረጋል፣
 • በአገር አቀፍና በክልል ደረጃ የተጠጣመ የግዥና ንብራት አስተዳደር ስርዓት እንዲኖር የሚያስችል አሰራር ስርዓት ይዘረጋል፣
 • የስራ ዕቅድና የአፈጻጸም ሪፖርት አዘጋጅቶ ያቀርባል፣
 • የዳይሬክቶሬቱን ዓመታዊ፣ የሩብ ዓመት፣ የግማሽ ዓመት፣ የዘጠኝ ዓመት ዕቅድና የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቶችን ለቅርብ ኃላፊና ለቢሮ በተቀመጠዉ የጊዜ ገደብ ያቀርባል፣
 • ዳይሬክቶሬቱን በሚመለከቱ በተለያዩ ስብሰባዎች፣ሴሚናሮች ላይ በመገኘት የልምድ ልዉዉጦችንና ግንዛቤ በመቀመር በዳይሬክቶሬት ሥር የሚገኙ ባለሙያዎችን ዉጤታማ የሆነ ሥራ እንዲያከናወኑ ማድረግ፣የተገልጋዮችን እርካታ ደሰሳ ጥናት እንዲካሄድ በማድረግ የዳይሬክቶሬቱን አገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓት የሚሻሻልበት ሁኔታ ይቀይሳል፣
 • በዳይሬክቶሬቱ የሰዉ ኃይል በመዋቅሩ መሠረት እንዲሟላ ያደርጋል፣
 • በዳይሬክቴሩ የሚያስፈልጉ የሥራ ቁሳቁሶች እንዲሟላ ያደርጋል፣
 • የተቋሙን ዓመታዊ እቅድና በጀት በማዘጋጀት፣ አፈጻጸሙን በመከታተል፣ በመገምገም፣ የእቅድና በጀት ዝግጅትና አፈጻጸምን የሚያሻሽሉ ጥናቶችን በማካሄድ የመሥሪያ ቤቱን የእቅድና በጀት አፈጻፀም ውጤታማ እንዲሆን ያደረጋል፣ የእቅድና በጀት አፈጸጻምን ወቅታዊ ሪፖርት ያዘጋጃል ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፣
 • የተቀቋሙን ዓመታዊ እቅድና በጀት ያዘጋጃል፣ ይከልሳል፣ ያሻሽላል፣ ለበላይ ኃላፊ አቅርቦ ያጸድቃል፣ የተቋሙ ስትራቴጂክ እቅድ ሲዘጋጅና ሲከለስ አስፈላጊውን ግብአት ያሰባስባል፣ ያዘጋጃል፣
 • አዳዲስ የፖሊሲ ሀሳቦች ሲቀርቡ ከተቋሙ ኃላፊነትና ተግባር ጋር የሚዛመዱ መሆናቸውን ያረጋግጣል፣ አስተያየት ይሰጣል፣
 • ለእቅድና በጀት ማስፈጸሚያ የሚሆን የበጀት ፍላጎት ያዘጋጅል፣ ይጠይቃል የተፈቀደውን በጀት ለየሥራ ክፍሎች ይደለድላል፣
 • የሌሎች ሥራ ክፍሎችን እቅድና በጀት ዝግጅት ላይ ሙያዊ ድጋፍ ያደርጋል፣ የምክር አገልግሎት ይሰጣል፣
 • በእቅድና በጀት ዝግጅት ክትትልና ግምገማን በሚመለከት ለሥራ ክፍሉ ባለሙያዎችና ሌሎች እንደ አስፈላጊነቱ ስልጠና ይሰጣል፡፡
 • የመሥሪያ ቤቱን የእቅድና በጀት አጠቃቀም በእቅድ መሠረት መሆኑን ይከታተላል፣ በእቅድና በበጀት አጠቃቀም የሚከሰቱ የአፈጻጸም ችግሮችን በመለየት የሚፈቱበትን የውሳኔ ሀሳብ ለኃላፊው ያቀርባል፣
 • በመሥሪያ ቤቱ የተዘጋጀውን ዓመታዊ እቅድና በጀት አፈጻጸም ይከታተላል ይገመግማል ግብረ-መልስ ይሰጣል፣
 • የተመደበው እቅድና በጀት በፕሮግራሙ መሠረት ለተፈለገው ሥራ መዋሉን ይከታተላል፣ ችግር ሲያጋጥም የማስተካከያ እርማጃ እንዲወሰድ ያደርጋል፣
 • የእቅድና በጀት እጥረት ሲያጋጥም የበጀት ምንጭ የሚገኝበትን አማራጭ ሀሳብ ለኃላፊው ያቀርባል፣ የበጀት ዝውውር ሲፈቀድ ተግባራዊ ያደርጋል አፈጻጸሙን ይከታተላል፣
 • ከጥናት ከግምገማና ወቅታዊ ጉዳዮች የመነጩ መረጃዎችን ጥልቅ ትንተና በማካሄድ ተግባራዊ እንዲሆን ያደርጋል፣ አፈጻጸሙን በመከታተል የውሳኔ ኃሳብ ለበላይ ኃላፊው ያቀርባል፣
 • የእቅድና በጀት ዝግጅት ሥራ የሚሻሻልበትን ሁኔታ በተመለከተ ጥናት ያደርጋል፣ ምርጥ ተሞክሮዎችን በማሰባሰብ ይቀምራል ለውሳኔ
 • የተቋሙን በተጨማሪ የተፈቀደ በጀት በሥራ ሂደትና በወጪ መደብ በመለየት የተስተካከለ ምዝገባ ሌጀር ላይ ያከናውናል፣ በግማሽ አመት የበጀት ዝውውር ጥያቄ በመቀበል ያጣራል፣ በየሩብ ዓመት የዝውውሩን የተስተካከለ ምዝገባ ሌጀር ላይ ማከናወኑን ይከታተላል፣ ይገመግማል፣
 • የተቋሙን የቀጣይ ሦስት ዓመት የመንግስት ወጪ/ኢንቨስትመንት ፕሮግራሞች (መወፕ/መኢፕ) ዕቅድ ለሥራ ሂደቶች በማቅረብ አስተያይቶችን በመሰብሰብ የተሰጡ አሰተያየቶችን በማካተት ዕቅዱን ለተቋሙ ማኔጅመንት በማቅረብ ያሰተቻል፣ የተሰጡ ግበአቶችን ያካትታል፣ ያፀድቃል፣
 • ተቋሙን ዓመታዊ የመንግሥት በጀት ዝግጅት የሚያስፈልጉ የፖሊሲ ዶክመንትና የጥናት ውጤቶችን መረጃ በማሰባሰብና በማደራጀት በጀት ያዘጋጃል፣ያሰተዳድራል፣ ወቅቱን ጠብቆ ለሥራ ሂደቶች የበጀት ጥሪ ያስተላልፋል፣ ይከታትላል፣
 • በክልሉ መንግስት የበጀት አዋጅ ለተቋሙ የፀደቀውን መደበኛ ጥቅል በጀት (Block Grant) ለሥራ ሂደቶች ረቂቅ የበጀት ድልድል በማዘጋጀት ለማኔጅመንት ያቀርባል፣ በማኔጅመንት የፀደቀውን የሥራ ሂደቶች መደበኛና ካፒታል በጀት ለሥራ ክፍሎች በደብዳቤ ያሳውቃል፣ አፈጻጸሙን ይከታትላል፣ ይገመግማል፣
 • የተቋሙን የፀደቀ በጀት በሥራ ሂደትና በወጪ መደብ ትክክለኛነታቸውን በማረጋገጥ ማጽደቅና የማሳወቅ ተግባራቶችን ማለትም የድርጊት መርሃ ግብር (Action Plan)፣ የጥሬ ገንዘብ ፍላጎት መርሃ ግብር (Cash Request)፣ የማዘጋጀት፣የማስተላለፍና የመከለስ ሥራዎችነ ያከናውናል፣
 • የተቋሙን የበጀት ዝውውር መረጃና የተስተካከለ በጀት መረጃ በዝርዝር በካፒታልና በመደበኛ በጀት ትክክለኛነታቸውን መርምሮ ያረጋግጣል፣
 • የተቋሙን የበጀት ዓመት ይፈጥራል/ Create Budget Year/ ፣ የበጀት መዋቅር ያሰተካክልል /Edit Budget Structure/፣ የበጀት መዋቅር ያጠፋል /Delete Budget Structure/ እና የበጀት መዋቅር ማሻሻያ ሀሳብ ለሥራ ሂደቶቹ ያቀረባል፣ በጀት ያስተዳደርል፣ ይከታትልል፣ ይገመግማል፤
 • የተቋሙን ዓመታዊ በጀት በበጀት ኮድና በየሥራ ሂደቱ (ወጪ ማዕከሉ) በመዘርዘር ማዘጋጀትና ያጠቃልላል፣ የበጀት መረጃ ሥርዓት ያስተዳደርል፣
 • የቢሮውን ገቢ በጀት መረጃ በፋይናንስ ምንጭ (ከመንግስት ግምጃ ቤት፣ የውስጥ ገቢ፣ ብድርና እርዳታ)፤ የወጪ በጀት መረጃ የወጪ መደብ ትክክለኛነት በፋይናንስ ምንጭ እንዲሁም በካፒታልና በመደበኛ ወጪ እና ከብድር እና እርዳታ የሚገኝ በጀት በትክለኛው የአበዳሪ ወይም ረጂ ድርጅት ኮድ የተመዘገበ መሆኑን በማረጋገጥ በዝርዝር በአይቤክስ ሲስተም ይመዘግባል፣ አፈጻጸሙን ይከታትላል፣
 • የተቋሙን ዓመታዊ የካፒታልና መደበኛ በጀት በአይቤክስ ሲስተም ያስጸድቃል /Approve the Budget/፣ የፀደቀ በጀት ወደኋላ ይመልሳል /Demote the Approved Budget/፣ የበጀት ማስተካከያ ያስተዳድራል፣
 • የተጨማሪ በጀትና የበጀት ዝውውር መረጃ የተስተካከለ በጀቶችን መረጃ በዝርዝር በካፒታልና በመደበኛ በጀት ትክክለኛነታቸውን መርምሮ ማረጋገጥና ለውሳኔ ማቅረብ
 • የተቋሙን ዓመታዊ በጀት መረጃ በሥራ ሂደትና በወጪ መደብ በፋይናንስ ምንጭ ያጠቃልላል፣ የበጀት መረጃ ስርዓት ያስተዳድራል፣ የእቅድ አፈፃፀም የሩብ፣ የግማሽ ዓመትና ዓመታዊ ክትትልና ግምገማ ያደረጋል፣ የሥራ ሂደቶች አፈፃፀም ሪፖርት በመቀበል በማጠቃለል፣ ለማኔጅመንት ያቀረባል፣ ግብረ መልስ ይሰጣል፤
 • የተቋሙን የአምስት ዓመት ልማት እቅድ አፈፃፀም የእኩሌታ ጊዜ ግምገማ በማካሄድ ሪፖርት ያዘጋጃል፣ የግምገማ ውጤት ላይ በመመስረት እቅዱን ይከልሳል፣ የአምስት ዓመት የልማት እቅድ አፈፃፀም የማጠቃለያ ጊዜ ግምገማ በመገምገም ሪፖርት ያዘጋጃል፣ የቀጣይ የአምስት ዓመት ልማት እቅድ እንዲዘጋጅ ስራ ሂደቶችን ያስተባብራል፤
 • የተቋሙን የሥራ ሂደቶች የለውጥ/የሪፎርም/ ሥራዎችን ያስተባብራል፣ ይከታትላል፣ ሪፖርት በመቀበልና ግብረ መልስ ይሰጣል፣ የተቋሙ የለውጥ ሥራዎች አፈፃፀም ለፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ ሪፖርት ያቀረባል፤
 • በቢሮው የሚደረጉ የአቅም ግንባታ ተግባራት ፍላጎት ከሁሉም ዳይሬክቶሬቶችና ዘርፎች በመቀበል ያደረጃል፣ የተደራጀውን የአቅም ግንባታ ተግባራት በመተንተን ከበጀት ጋር አላይን ያደርጋል፣ ሁሉም የአቅም ግንባታ ተግባራት በወቅቱ እንድተገበሩ ያማክራል፣ ይከታትላል፣
 • በቢሮው ውስጥ የሚተገበሩ የአቅም ግንባታ ተግባራትን በአካል በመገኘት ይከታትላል፣ መረጃ በመሰብስብ፣ በመተንተን፣ ዕርካታና ክፍተት/Gap/ ይለያል፣ በተለየው መረጃ ላይ በመመርኮዝ የሚመለከታቸው አካላት አስፈላጊውን ስራ እንድሰሩ መረጃዎችን አደራጅቶ ለማነጅመንት በማቅረብ ውሳኔ ያሰጣል፡፡

ለዘርፉ የተሰጠውን ተግባርና ኃላፊነት ለመወጣት ባለ በጀት መ/ቤቶች ውስጥ የሚገኙ የውስጥ ኦዲተሮችን ማደራጀትና የአቅም ግንባታ ስራዎችን ማከናወንን የሚያካትት ሲሆን በስሩ በተደራጁት ዳይሬከተሮች አማካይነት የክልሉን መንግስት የፋይናንስና ንብረት ኢንስፔክሽን ማከናወን፣ እርምጃ መውሰድና እንድወሰድ ማድረግ ተግባራቶችን ያከናውናል፡፡

 • መ/ቤቶች የውስጥ ኦዲት የአሰራር ችግሮች በጥናት እንዲለዩ ያደርጋል፡፡
 • የውስጥ ኦዲትን የሚመለከቱ በባለሙያዎች የሚቀርቡ የፖሊሲ ሃሳቦችን ይገመግማል፤ማሻሻያ በማድረግ ያጠቃልላል፡፡
 • የውስጥ ኦዲት አሠራር በተመለከተ በባለሙያዎች የሚቀርቡ አዳዲስ የአሰራር ስርዓቶች፣ መመሪያዎችንና ማንዋሎችን ይገመግማል፤ማሻሻያ በማድረግ እንዲጸድቅ ያደርጋል፤፤
 • ከውስጥ ኦዲት ጋር ተያያዥነት ያላቸውን በዓለምና አገር አቀፍ ምርጥ ተሞክሮዎችን እንዲካሄዱ አሰፈላጊውን ነገር ያመቻቻል፡፡
 • በባለበጀት መ/ቤቶች አሰራሮች ውጤታማ የሆነ የውስጥ ኦዲት አደረጃጀት ለመፍጠር የሚካሄዱ ጥናቶችን በበላይነት ያስተባብራል፤የሚቀርቡ የጥናት ውጤቶችን ይገመግማል፤ማሻሻያ በማድረግ ያጸድቃል፡፡
 • የውስጥ ኦዲት በሥራው ምክንያት የሚደርስበትን ተጽእኖ እንዲጣሩና መፍትሄ እንዲያገኙ ያደርጋል፡፡
 • የውስጥ ኦዲት አሰራርን በተመለከተ የበላይ ኃላፊዎችና ለሚመለከታቸው ባለሙያዎች የተለያዩ የግንዛቤ ማስጫበቻ ስልጠናዎችና የውይይት መድረኮች እንዲዘጋጁ አስፈላጊውን ነገር ያመቻቻል፡፡
 • ከሙያና ከስልጠና ተቋማት ስልጠናዎችን ለማግኘት የሚያስችሉ ፕሮጀክት እንዲቀረጹ ያደርጋል፤ ስልጠናዎችንም ያፈላልጋል፣የኦዲት እቅድ ዝግጀት እና የስጋት አካባቢዎችን የመለየት የሚደረጉ ጥናቶችን ያስተባብራል፤ በበላይነት ይመራል፡፡
 • በተቋማት የአስተዳደር ሥርዓት /Governance/ እንዲገመገም ያደርጋል፡፡
 • በተለዩት የስጋት አካባቢዎች መስረት የፋይናሻል፣ የሕጋዊነትና የክዋኔ ኦዲት እንዲሁም የውስጥ ቁጥጥር ሥርዓት ግምገማ እንዲከናወኑ ያደርጋል፤ሂደቱንም በበላይነት ያስተባብራል፤ይመራል፤
 • በባለሙያዎች የሚቀርቡ የፋይናሻል፣ የሕጋዊነትና የክዋኔ ኦዲት እንዲሁም የውስጥ ቁጥጥር ሥርዓት ግምገማ የኦዲት ሪፖርቶች በመገምገም እንዲጠቃለሉ ያደርጋል፡፡
 • በኦዲት መውጫ ስብሰባ ላይ በመገኘት ስብሰባውን ይመራል ያወያያለ፤
 • በውይይቱ ወቅት በተደረሰባቸው ስምምነቶች መሠረት ተዘጋጅቶ የቀረበለትን የኦዲት ሪፖርት ትክክለኛነት አረጋገጥ ያስተላልፋል፤
 • ለተቋማት አመራሮችና የውስጥ ኦዲተሮች በመንግሥት ፋይናንስ አስተዳደር ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ የማማከር አገልግሎት ይሰጣል፡፡
 • የውስጥ ኦዲት አሠራር በተመለከተ የተዘጋጁ አዳዲስ የአሰራር ስርዓቶችን፣ መመሪያዎችንና ማንዋሎችን በአግባቡ ተግባራዊ መደረጋቸውን ክትትልና ቁጥጥር መደረጉን ይከታተላል፤ይቆጣጠራል፤
 • ከመንግስት መስሪያ ቤቶች የሚቀርቡ የውስጥ ኦዲት እቅዶችንና ሪፖርቶችእንዲገመገሙ በማድረግ የማሻሻያ ሃሳቦችንለተቋማት ይልካል፡፡
 • መ/ቤቶች ኦዲቱ ሲከናወን በተዘጋጀው የኦዲት ፕሮግራም መሰረት ሥራው እየተከናወነ መሆኑን ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፤
 • በውስጥና በውጪ ኦዲተሮች በተሰጡ የኦዲት አስተያየትና ማሻሻያ ሃሳቦች መሰረት የተወሰዱ የእርምት እርምጃዎች በአግባቡ መገምገሙንይከታተላል፤ይቆጣጠራል፡፡
 • በባለሙያዎች የሚቀርቡ የመ/ቤቶች የተጠቃለለ የውስጥ ኦዲት ሪፖርት ይገመግማል፤ማሻሻያ በማድረግና በማጸደቅ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት እንዲላክ ያደርጋል፡፡
 • በመ/ቤቶች አንኳር የኦዲት ግኝቶች ሪፖርት ላይ ተመስርቶ በሚኒስትሮች ምክር ቤት የተሰጠ አመራር ተፈጻሚነትን ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤
 • የውስጥ ኦዲት ክትትልና ድጋፍ በተመለከተ ለባለሙያዎች የተሰጡ ስልጠናዎች የመጡትን ለውጥ ይከታተላል፤ይገመግማል፣
 • ወቅታዊ ስራ አፈጻጸም ሪፖርት  ያቀርባል

ቻናል አንድ ፕሮግራሞች የመንግሥት የልማት ዉጥኖች ከግብ ለማድረስና ድህነትን ከሀገሪቱ ለማስወገድ የሚደረገዉን የመንግሥት የልማት እንቅስቃሴዎችን ጥረት በማገዝ ረገድ ከዉጭ ሀገር የሚገኘዉ ዕርዳታና ብድር የሚጫወተዉ ሚና በቀላሉ የሚገመት አይደለም፡፡ መንግሥት በዉጭ እርዳታና ብድር ሀብትን ለማገኘት በሀገሪቱ የተቀረፀዉን የመንግሥትን ፖሊስ ለማስፈፀም የሚያግዙ በግብርና፣ በትምህርት፣ በጤና፣በዉሃ፣ በመንገድ፣ በከተማ አስተዳደር፣ በሴቶች፣ በወጣቶች፣ በህፃናት እና በሌሎችም ዘርፍ የተለያዩ ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶችና በማዘጋጀትና በመቅረጽ ከተለያዩ አለም አቀፍ ድርጅቶችና መንግሥታት ጋር የዉል ስምምነት በመፈራረም የተቀመጡ የዉጤት አመልካቾችን መነሻ በማድረግ የመደበኛ በጀት ክፍተት የሚሸፍን ተጨማሪ ሀብት በመገኘት የልማት ሥራዎችን በማፈጠን ላይ ይገኛል፡፡ በዚህ ሁኔታ ከ1997 ዓ/ም ጀምሮ በድህነት ቀናሽ መሥሪያ ቤቶችና በሌሎችም መንግሥት መሥሪያ ቤቶች ከክልል እስከ ወረዳ/ቀበሌ ድረስ የሚተገበሩ የተለያዩ ፕሮግራሞችንና ፕሮጅክቶችን በመቅረፅ በርካታ ሀብት ተግኝቷል፣ እየተገኘም ይገኛል፡፡ ለአብነት የገጠር ልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም፣ የከተማ ልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም፣ የከተሞች መሠረተ ልማትና ማስፋፊያ ፕሮግራም፣ የከተሞች ተቋማዊና መሠረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም፣ የመሬት ይዞታና ሰርትፍኬት አሰጣጥ ፕሮግራም፣ የትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም፣ የመንግሥት ፋይናንስ አስተዳደር ፕሮጅክት፣ የእንቨስተመንት ፕሮጀክት ፋይናንስንግ፣ የፍትሃዊ መሠረታዊ አገልግሎት ለሁሉ አቀፍ የዕድገት ተጠቃሚነት ፕሮግራም፣ የገጠርና የከተማ የመጠጥ ዉሃ ሃይጂንና ሳንቴሽን ፕሮግራም፣ የማህበረሰብ ትግበራ የገጠር የመጣጥ ዉሃ ፕሮግራም፣ የፋይናንስ ግልጽነትና ተጠያቂነት ፕሮጅክት እና ሌሎችም ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች ከክልሉ እስከ ወረዳ ድረስ የሚተገበሩ ናቸዉ፡፡

አብዘኞዎቹ ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች ሥራ ከጀመሩ ከ12 ዓመት በላይ ዕድሜ ያላቸዉ ሲሆኑ ጥቅቶቹ ከ7 ዓመት በላይ የቆዩ ናቸዉ፡፡ አንዱ ፕሮግራም በሌላ ፕሮግራም እየተተካ የሚሄድ ነወ፡፡ የፕሮግራሞች ዋና ዓላማቸዉም የመንግሥትን የልማት ሥራዎችን እንዲፋጣኑ በማድረግ ለህብረተሰቡ የሚሰጠዉ አገልግሎት አሰጣጥ ወቅታዊ፣ ጥራት ያለዉና ግልጽ እንዲሆን በማድረግ ተጠያቂነት የሰፈነበት የአሰራር ሥርዓት ማጠናከር ነዉ፡፡ የበጀት ምንጫቸዉም ዕርዳታ፣ ብድር፣ የመንግሥት መዋጮ እና የህብረተሰብ ተሳትፎ ናቸዉ፡፡ ከእነዚህም ምንጮች በፋይናንስ ቢሮ ለፕሮግራሞቹ ሀበት አስተዳደር ወደ ተከፈቱ ባንክ አካዉንቶች የሚፈሰዉ ለፕግራሞቹ ተጠቃሚዎች በሚደርሰዉ በቻናል አንድ የገንዘብ ፍሰት ነዉ፡፡ ቻናል አንድ በመባል የሚታወቀዉ የፈንድ ፍሰት ከለጋሽ አካላት የሚገኝ ገንዘብ በቀጥታ በፌዴራል ገንዘብ ሚኔስቴር ሂሳብ ዉስጥ ገብቶ ወደ ክልል ፋይናንስ ቢሮ በፕሮግራሞች ባንክ አካዉንት ገቢ ሆነዉ ከነዚህ ባንክ አካዉንቶች በሚቀርበዉ በጥሬ ገንዘብ ፍላጎት መርሃ ግብር መሠረት የጥሬ ገንዘብ ዝዉዉር እየተፈፀመ አፈጻጸሙ ድጋፍ፣ ክትትልና ግምገማ እየተደረገበት የሚከናወን ነዉ፡፡ ይህ የቻናል አንድ ፕሮግራሞች ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት በመንግሥት ፋይናንስ አስተዳደር ዘርፍ ሥር ከሚገኙ ዳይሬክቶሬቶች ዉስጥ አንዱ ሲሆን በዳይሬክቶሬቱ ሥር በርካታ ቡድኖች ይገኛሉ፡፡ እነርሱም የልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም ቡድን፣ የዋን ዋሽ ናሽናል ፕሮግራም ቡድን፣ የአጠቃለይ የትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም ቡድን፣ የከተሞች መሠረተ ልማትና ማስፋፊያ ፕሮግራም ቡድን፣ የኮ.ዋሽ ፕሮግራም ቡድን፣ የመሬት ይዞታና ሰርትፍኬት አሰጣጥ ፕሮግራም ቡድን፣ የመንግሥት ፋይናንስ አስተዳደር ቡድን፣ የከተማ አስተዳደር ልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም ቡድን እና የፋይናንስ ግልጽነትና ተጠያቂነት ፕሮግራም ቡድን ናቸዉ፡፡
የፕሮግራሙ ተጠቃሚዎችም ከክልል እስከ ወረዳ ድረስ የኢኮኖሚ ዘርፍ መንግሥት መሥሪያ ቤቶች፣ የማህበራዊ ዘርፍ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች እና የአስተዳደርና አገልግሎት ዘርፍ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ናቸዉ፡፡

 • ከመንግስት የሚተላለፉ የፋይናንስ ሕጎች፣ ደንቦችና መመሪያዎች በአግባቡ ሥራ ላይ መዋላቸውን ይቆጣጠራል፣ አስተማማኝና ለቁጥጥር አመቺ የሆነ የሂሣብ አያያዝ ስርዓት እንዲኖር ያደርጋል፤
 • የፋይናንስ፣ የበጀትና የሂሣብ አያያዝ ተግባራት በሂሣብ አሠራር መርሆዎችና ደንቦች መሠረት መከናወናቸውን ያረጋግጣል፤
 • ከየዘርፉ የሚቀርቡ የግዥና የክፍያ ጥያቄዎችን አስፈላጊነት በማጥናት  የግዢ ሰነዶች፣ የክፍያ ቼክና ማዘዣዎችን በፊርማው ያጸድቃል፣
 • የየሥራ ክፍሉ የግዢ ጥያቄዎች ከንብረት ክምችት መጠን ጋር እንዲመሳከርና ከተመደበው በጀት ጋር ተጣጥሞ የጨረታ ሰነድ እንዲዘጋጅና እንዲሰራu ያደርጋል፣
 • የፀደቀ ግዢን ተፈላጊ ፎርማሊቲዎችን በማሟላት ያስፈፅማል፣ ለውጭ አገር ዕቃዎች ግዢ የባንክ ሌተር ኦፍ ክሬዲት መከፈቱን፣ የመድህን ዋስትና መገባቱን ያረጋግጣል፣ ዕቃው ሀገር ውስጥ መግባቱንና ከጉምሩክ ወጪ መደረጉን ያረጋግጣል፤
 • የቋሚና የአላቂ ዕቃዎች አያያዝና አስተዳደር ተግባራት በመንግሥት የአሠራር ደንቦችና መመሪያዎች መሠረት መፈፀማቸውን ያረጋግጣል፣ ሰነዶች በትክክል መመዝገባቸውንና መቀመጣቸውን ይቆጣጠራል፣
 • ተገቢው የንብረት ገቢ፣ ወጪና ዝውውር መከታተያና መቆጣጠሪያ መዝገቦችና ካርዶች መያዛቸውን ያረጋግጣል የግዢ፣ የንብረት አስተዳደርንና ቁጥጥር ሥራን ለማሻሻል የሚያስችሉ የአሠራር ዘዴዎችን እያጠና ሀሳብ ያቀርባል፣ ሲፈቀድ ስራ ላይ እንዲውል ያደርጋል፣
 • የቋሚና የአላቂ ዕቃዎች መዝገብ እንዲያዝ ያደርጋል፣ የዕቃዎች ገቢ ወጪና ዝውውር በዓይነት፣ በስም፣ በመጠንና በዋጋ ተለይተው መመዝገባቸውን ይቆጣጠራል፣ የክምችት ዕቃዎችን ከወጪ ቀሪ ተቀናንሶ እንዲያዝ በማድረግ የዕቃዎችን የክምችት መጠን ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፤
 • የንብረት ቆጠራን ያስተባብራል፣ በንብረት አያያዝና ክምችት ላይ የኦዲት ሪፓርቶችን ተግባራዊነት ይከታተላል፤የበጀት የግዥ የፋይናንስና የንብረት አፈጻጸምና የስራ ፍሰት የግንኙነት ሰንሰለት   የቁጥጥር ስርአት ይዘረጋል፡፡
 • መጋዘኖች በዘመናዊ የዕቃና የንብረት አያያዝ መሠረት መደራጀታቸውን፣ ለቁጥጥር ግልፅና አመቺ በሆነ ሁኔታ መሰራታቸውን ያረጋግጣል፤ከውጭ አገር መንግስታትና አለም አቀፍ ድርጅቶች በልዩ ልዩ መልክ የሚሰጥ ብድርና እርዳታ በተመለከተ ጉዳዩ ከሚመለከተው የስራ ሂደት ጋር በመሆን ሂሳቡ እንዲመዘገብ ያደርጋል ፡፡
 • የትራንዝአክሽን የሂሣብ መግለጫዎችን፣ የሂሣብ ሚዛንና ትንታኔ ያዘጋጃል፣ የመ/ቤቱ ገቢዎች በወቅቱ መሰብሰባቸውንና ግዴታዎች በጊዜ ገደብ ውስጥ መከፈላቸውን ያረጋግጣል፤
 • የበጀት እጥረት ሲያጋጥም ተጨማሪ በጀት ያስፈቅዳል
 •  ከተለያዩ ተቋማት እና ከአቅራቢዎች ጋር የግዥ፣ የፋይናንስና የንብረት  ውል ይዋዋላል ተግባራዊነቱን ይከታተላል በውሉ መሰረት ያልፈጸሙትን ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ለሚመለከተው አካል ያስተላልፋል
 • ጥሬ ገንዘብንና በባንክ ያለውን ሂሣብ በየጊዜው እያስመረመረ የመ/ቤቱ የገንዘብ አቅም እንዲታወቅ ያደርጋል፣ ጉድለት ሲኖር ተገቢ እርምጃ ይወስዳል፤
 • የመስሪያ ቤቱ ገቢ ለተፈቀዱና ለተገቢው ሥራ መዋላቸውንና በአግባቡ መመዝገባቸውን ይቆጣጠራል፤ ለዕቅድ አዘገጃጀት የሚረዱ መግለጫዎችን ያዘጋጃል፤ ማስተካከያ እርምጃ ይወስዳል፤
 • ሂሣብ በወቅቱ እንዲዘጋና በውጭ ኦዲተሮች እንዲመረመር ያደርጋል፣ ሪኦዲተሮች በተጠቆሙ ድክመቶች ላይ ለመስሪያ ቤቱ የውስጥና የውጪ ኦዲተሮች የሂሳብ መዛግብት ቀርቦ ሒሳቡን በማስመርመር አስፈላጊውን መተማመኛ እንዲሰጥ ያደርጋል ፣የኦዲት ሪፖርቱን መሰረት በማድረግ ሊታረም ወይም ሊሻሻል የሚገባውን በወቅቱ እንዲሻሻል ያደርጋል፣
 • የተቋሙን አደረጃጀትና የተለያዩ የሰው ሀብት ሥራ አመራር ጥናቶችን በየጊዜው በማጥናት ደንብና መመሪያን መሠረት በማድረግ የተቋሙን ዕቅድና ዓላማ ሊያሳካ የሚችል የሰው ሀብት እንዲሟሉ ያገርጋል፤
 • አዲስ የሰው ኃይል ፍላጎት ለሚያቀርቡ የሥራ ክፍሎች እንደ አስፈላጊነቱ ጥናት በማካሄድና የሥራ ደረጃውን በመወሰን ለሚመለከተው ተቋም ያቀርባል፣ ሲፈቀድም በደንቡ መሠረት ይፈጽማል፣
 • በተቋሙ አደረጃጀት መሠረት በየሥራ መደቦች ተገቢው የሥራ ዝርዝር እንዲዘጋጅ በማድረግና በመገምገም የማሻሻያ ሃሳብ ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፣ተፈጻሚነቱንም ይከታተላል፣
 • በተቋሙ የተለያዩ የሰው ሀብት ሥራ አመራር መመሪያዎችና ማኑዋሎችን ያዘጋጃል፣ ተፈጻሚነቱን በመከታተል እንዲሻሻል ያደርጋል፣
 • የተቋሙ ድርጅታዊ መዋቅር በሚሻሻልበት ጊዜ ጥናት በማድረግና ለሚመለከተው ያቀርባል ሲፈቀድ ተገቢውን በማሟላት ሥራ ላይ እንዲውል ያደርጋል፣
 • የሰው ኃይል እቅድ መረጃዎችን ያደራጃል፣ ያጠናቅራል፣ ከሌሎች ሙያተኞች ጋር በመተባበር የተቋሙን አደረጃጀት ያጠናል፣
 • ከተቋሙ በሚደርሰው የሰው ኃይል ፍላጎት መጠየቂያ ቅጽ መነሻ በማድረግ ለቅጥር፣ ለደረጃ ዕድገትና ለዝውውር ደንብና መመሪያ መሠረት በማድረግ ማስታወቂያ ያወጣል፣
 • በማስታወቂያ መሠረት የተመዘገቡ አመልካቾችን መረጃ ያጣራል፣ ምርጫ እንዲከናወን በማድረግ ያጸድቃል፣
 • ፈተና በማዘጋጀት ወይም እንዲዘጋጅ በማድረግ ተወዳዳሪዎችን በመፈተን የፈተናውን ውጤት ያሳውቃል፣
 • የተቀጠሩ ሠራተኞች የተቋሙንና የመንግስት ሠራተኞች አዋጅ፣ ደንቦችና መመሪያዎችን እንዲያውቁ ያደርጋል፣
 • በተቋሙ የተወሰዱ አስተዳደራዊ እርምጃዎች ህግንና መመሪያዎችን መሠረት ያደረጉ መሆናቸውን ያረጋግጣል፡፡
 • በተቋሙ ላሉ ሠራተኞች የአገልግሎትና ልዩ ልዩ ጭማሪ የሚገባችውን ሠራተኞች በመለየትና በጀት እንዲያዝላቸው በማድረግ ተፈጻሚነቱን ይከታተላል፣
ቴክኖሎጂ ለአንድ ሃገር ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኀበራዊ ዕድገት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከምንም በላይ መሆኑን ዛሬ ላይ የስልጣኔ ጫፍ የደረሱ ፣ የበለፀጉና የዓለማችን ሃያላን ተብለው የሚጠሩ አገሮች ምሥክሮች ናቸው፡፡ ይህም በመሆኑ መንግሥት የሃገራችን ሕዝብ የዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ እንዲሆንና የቴክኖሎጂው ሽግግር ከጫፍ እንዲደርስ ተግቶ በመሥራቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ ቀላል የማይባል የሃገራችን ሕዝብ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ መሆን ችሏል፡፡

ምን ይሰራል?

 1. የፋይናንስ ሲስተም ሶፍተዌሮችን ያስተዳደራል
  • የለሙ የፋይናንስ ሲስተሞች/ሲስተም ሶፍትዌሮች/
  • IBEX (Integrated Budget and Expenditure)፣
  • IFMIS (Integrated Financial Management Information System)
  • DEVInfo /Development Information System/
  • Payroll System ፣
  • Inventory System ፣
  • Form Tracking System፣
  • Personnel Management System
  • Suppliers Management System
2. የመረጃ መረብ /Network/ ይዘረጋል፣ ያስተዳደራል
  • በቢሮ ውስጥ ያለውን ኔትወርክ
  • IBEX and IFMIS VPN /Virtual Private Network/ (Woredanet)
 1. ድረ-ገፅ ያለማል፣ ያሻሽላል፣ ያስተዳድራል፣
 2. በፋይናንስ ሲስተም ሶፍተዌሮች ላይ ሥልጠና ይሰጣል፣
 3. የኢኮቴ መሣሪያዎች ጥገና ያደርጋል፣
 4. በፋይናንስ ሲስተም ሶፍተዌሮች ላይ ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል
 5. የኢኮቴ መሣሪያዎች የግዥ ዝርዝር መሥፈርት (Specification ) ያዘጋጃል፣ የዕቃ አቅረቢው ሰነድ በተዘጋጀው Specification መሠረት መሆኑን ያጣራል፣ ያሸናፊ ድርጅት ያቀረበውን ዕቃ የቴክኒክ ምርመራ በማድረግ ያረጋግጣል፣
 • የተቋሙ የበላይ ኃላፊ የቃል አቀባይ ኃላፊ ሚና እንደተጠበቀ ሆኖ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው የቃል አቀባይነት ሥራን ይሰራል፣
 • የሕዝብ ግንኙነት ክፍል የተቋሙ ስትራቴጂያዊ ዓመታዊ የኮሙኒኬሽን ዕቅድ ከመንግስት ኮሙኒኬሽን ስትራቴጂያዊ ዕቅድ ጋር አጣጥሞ ማዘጋጀት ለተቋሙ ሥራ አመራር አቅርቦ ማጽደቅ፣ ለመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ማሳወቅና ተግባራዊ ማድረግ፣
 • በተቋሙ አስፈላጊውን ሙያዊ ብቃትና ሥነ-ምግባር ያለው የሕዝብ ግብኙነት ባለሙያ እንዲፈጠር፣ እንዲስፋፋና እንዲዳብር የተለያዩ አቅም ግንባታ ሥልጠናዎች እንዲሰጡ ማቀድ፣ በሚመለከተው አካል ሲፈቀደም ተግባር ላይ ያውላል፣
 • ከመሥሪያ ቤቱ ፖሊሲ፣ ስትራቴጂ፣ ፕሮግራም ዕቅዶችና አፈፃፀሞች ጋር ተያያዥነት ያላቸው መልዕክቶች በመቅረፅ በተቋሙ የሥራ አመራር አቅርቦት በማፅደቅ በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች ማሰራጨት፣ ግብረመልስ ማሰባሰብ፣
 • መስሪያ ቤቱን በተመለከቱና ተያያዥነት ባላቸው ጉዳዮች ዙሪያ የሚዲያ ዘገባ ክትትል በማድረግ ትንተና በማዘጋት ለበላይ ኃላፊ በማቅረብ የኮሙኒኬሽን ሥራን ማማከር፣
 • የመስሪያ ቤቱ መረጃዎች በአግባቡ የሚሰበብቡበትን የሚደራጁበትን ሥርዓት መዘርጋትና ለሚዲያና ለማንኛውም አካል የመረጃ ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ መስጠት ወይም አግባብ ካላው የተቋሙ አካላት ምላሸ እንዲሰጥበት ማድረግ፣
 • በተለያ ጊዜያት ከመንግስት የሚወጡ ወቅታዊ መልዕክቶችን ተቀብሎ ለህዝብ ግንኙነት ስራው ጥቅም ላይ ማዋል፣
 • በህብረተሰቡ፣ ባለድርሻ አካላትና በተቋሙ መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር እንዲቻል የተለያዩ የሕዝብ ግንኙነት ሥራዎችን በማቀድ ተግባራዊ ማድረግ፣
 • በመስሪያ ቤቱ ፖሊሲዎች፣ ደንቦች፣ ስትራቴጂዎችና መመሪያዎች እንዲሁም ለብሔራዊ መግባባት እና ለገጽታ የሚረዱ ልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ ግንዛቤ ማስጨበጥና ግልጸኝነትን ለመፍጠር የውይይት መድረኮች ማዘጋጀትና ማስተባበር፣
 • በመስሪያ ቤቱ ፖሊሲዎች፣ ደንቦች ስትራቴጂዎችና መመሪያዎች እንዲሁም ለብሔራዊ መግባባት እና ለገጽታ ግንባታ የሚረዱ ልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ ግንዛቤ ለማስጨበጥና ግልጸኝነት ለመፍጠር የውይይት መድረኮች ማዘጋጀትና ማስተባበር፣
 • በመስሪያ ቤቱ የሥራ ሂደቶች መካከል ጠንካራ የመረጃ ልውውጥ ስርዓት መዘርጋት፣ ማስተባበር፣ ማስፈጸም፣
 • የመስሪያ ቤቱ የሥራ ኃላፊችና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ ጋዜጠኞች የመስሪያ ቤቱን የልማት እንቅስቃሴዎች አፈፃፀሞችና ክንውኖች እንዲጎበኙ ማቀድ ማስተባበርና ማስፈጸም፣
 • ለብሔራዊ መግባባትና ለገጽታ ግንባታ የሚረዱ ነባርና አዳዲስ ዋና ዋና ክልል አቀፍ፣ ሀገር አቀፍና የዓለም አቀፍ ሁነቶች ላይ እንዲሁም የፈጠራ ሁነቶችን ከመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ጋር በመመካከር ማቀድ ማዘጋጀትና ተግባራዊ ማድረግ፣
 • ከመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት በሚሰጠው አቅጣጫ መሠረት እንደአስፈላጊነቱ የመስሪያ ቤቱን ፖሊሲዎች፣ ስትራቲጂዎች፣ እቅዶች፣ ፕሮግራሞች እና ፕሮጀክቶችን ለማስተዋወቅ የሚያስችሉ የሬዲዮና የቴሌቭዥን ፕሮግራም ዝግጅቶችን ያቅዳል፣ ያደራጃል ያስፈጽማል፣
 • በተቋሙ ድረ-ገፅ ላይ የሚጫኑ መረጃዎች ይዘት የመንግስት ፖሊሲ፣ ስትራቴጂና የተቋሙን ተልዕኮ ያገናዘበና ወቅታዊ መሆኑን ያረጋግጣል፤ ከመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ድረ-ገፅ ጋር በተመጋገበ መልኩ እንዲጫን ያደርጋል፣
 • የመስያ ቤቱን መረጃዎች በፎቶግራፍ በኦዲዮና ቪዲዮ ቀረጻና ህትመት በሥራ ክፍሉ እና በተባባሪዎች አማካኝነት ማዘጋጀትና ጥቅም ላይ ማዋል፣ ለሀገር ውስጥ ሚዲያዎች በየጊዜው መረጃዎችን አደራጅቶ መስጠትና እንደአስፈላጊነቱ የሥራ ትብብር ማድረግ፣
 • መስሪያ ቤቱን የሚመለከቱ የማስታወቂያ ሥራዎች በመንግስት በሚመጡ የማስታወቂያዎችና የስፖንሰርሺፕ ፖሊሲዎችንና መመሪያዎችን መሠረት ያደረጉ ለሕዝብ ግልጽ እና ትክክለኛ የሆነ መልዕክት ይዘው መውጣታቸውን እና ሥርጭታቸውንም የማስታወቂያ አዋጅ 759/2004ን መሠረት አድርጎ የተዘጋጀ መሆኑን ማረጋገጥ
 • በመስሪያ ቤቱ የሕዝብ ግንኙነት ሥራ ላይ ጥናት ማካሄድ፣ አስተያየት ማሰባሰብ መገምገም፣ አሰራሩ የሚሻሻልበትን አቅጣጫ መቀየስ እና ጥናቱ ተግባራዊ የሚሆንበትን ሁኔታ ማመቻቸት፣
 • በክልሉ እና በተቋም ደረጃ ያልተጠበቀ ክስተቶች/ቀውስ/ ሲፈጠር ወይም ሊከሰቱ የሚችሉ ክስተቶችን ቀውሶችን/ በመገንዘብ ማቀድና ተግባራዊ ማድረግ፣ ሌሎች አካላት ጋር በመመካከር መረጃ ማሰራጨትና የማረጋጋት ተግባር ማከናወን፣ በሶስት ወር የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት፣ የስድስት ወር፣ በዘጠኝ ወር እና በዓመት ወቅቱን ጠብቆ ለበላይ አካልና ለመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ማቅረብ፣ በተጨማሪም በተደራጀው የፌዴራል የሕዝብ ግንኙነት ፎረም ላይ ሪፖርቱን አቅርቦ በማስገምገም የሚሰጠውን ግብረ መልስ ተግባራዊ ማድረግ፡፡

ተገልጋዮች የመንግስት ኢንፎርሜሽን ሲጠይቁ ማሟላት የሚገባቸው ቅድመሁኔታዎች፡

 1. ኢንፎሜሽን ከጠየቁ መ/ቤቶች ወይም ድርጅቶች ህጋዊ ደብዳቤ ማቅረብ፣
 2. ተገልጋዮች የሚወስዷቸውን ኢንፎርሜሽን ከተሰጠበት ዓላማ ውጪ እንደማይጠቀሙባቸው ማረጋገጫ መስጠት፣
 3. የሥራ ሂደቱን ምስጢራዊ ኢንፎርሜሽን ለማይመለከታቸው ወገኖች አሳልፎ መስጠት የሌለበት መሆኑን ማመን፣
 4. ተገልጋዮች የሚወስዷቸውን መንግስታዊ ኢንፎርሜሽን ከተሰጠበት ዓላማ ውጪ ቢጠቀሙባቸው በሕግ ሊጠየቁ እንደሚገባ ማወቅ፡፡
 • የመ/ቤቱን የሥራ ባህል፣የአሠራር ስርዓቶች እና አደረጃጀቱን በየጊዜው ለማሻሻል የሚያስችሉ የለውጥ አጀንዳዎችን ይቀርጻል፣
 • ለመ/ቤቱ ተስማሚ የሆኑ ዘመናዊ የለውጥ ሥራ አመራርና የአሠራር ማሻሻያ ስልቶች ተለይተው እንዲቀርቡ ያደርጋል፤
 • የተቋማዊ ለውጥን ቀጣይነትን የሚያረጋግጡ አዳዲስ የአሠራር ስርዓቶች በማጥናት፣ ምርጥ ተሞክሮዎችን በመቀመር ለመ/ቤቱ ጠቃሚ የሆኑትን ተግባራዊ ያደርጋል፣
 • የሥራ ዘርፉን የአሰራር ችግሮች በመለየትና በማጥናት ምቹ የአሰራር ሂደት እንዲኖር ያደርጋል፣ተፈጻሚነቱን ያረጋግጣል፣  በተግባር ላይ እንዲውሉ የተመረጡ የለውጥ መሳሪያዎች አተገባበር ከሁኔታዎች ጋር ተጣጥመው እንዲሰራባቸው ስልት ይቀይሳል፣
 • በመ/ቤቱ የሚገኙ የሥራ ዘርፎች በአስቀመጡት ተቋማዊ የለውጥ ግቦች እና እቅድ መሠረት መፈጸማቸውን ይገመግማል፣ ክፍተት ካለው የመፍትሄ አቅጣጫ ያስቀምጣል፣
 • በመ/ቤቱ የመልካም አስተዳደር ሥርዓት መስፈኑን ያረጋግጣል፣አፈጻጸሙን ይገመግማል፣
 • በለውጥ አፈጻጸም ላይ የሚያጋጥሙ የአሠራር ችግሮችን ይለያል፣ስትራቴጂያዊ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል፣
 • በመ/ቤቱ ተግባራዊ የሆኑ የለውጥ መሣሪያዎች ያስገኙት ፋይዳ ይከታተላል፣
 • በሥራ ላይ እንዲውሉ ውሳኔ ያገኙ ልዩ ልዩ የጥናት ሰነዶች ተግባራዊ እንዲሆኑ ለተጠቃሚ ክፍሎች መተላለፋቸውንና ተግባራዊ መሆናቸውን ይከታተላል፣
 • ተቋማዊ ለውጥን ከአፈጻጸም አኳያ ለመገምገም በተዘጋጀ ሪፖርት አቀራረብ  ስርዓት ስለመቅረቡ ክትትል ያደርጋል፣ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ተቋማዊ ለውጥ  በቀጣይነት ለመተግበር እንዲችሉ የክህሎት፣ የአቅርቦት እና የአመለካከት ክፍተቶች የሚለይበት ስርዓት እንዲኖር ያደርጋል፣
 • የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ስለለውጥ ዓላማዎች  እንዲገነዘቡና የህዝብ አገልጋይነት ስሜት እንዲያዳብሩ የአመለካከት ለውጥ እንዲያመጡ ተከታታይነት ያላቸው የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች እንዲዘጋጁ ተግባራዊ እንዲሆኑ ያደርጋል፣
 • የሥራ ኃላፊዎች በስራቸው ያሉትን ፈጻሚዎች የማብቃት ሥራ እንዲያከናውኑ ያደርጋል፣ ይደግፋል፣የሥራ ዘርፉን ስትራቴጂክ እቅድ መሠረት በማድረግ ዓመታዊ እቅድ ተዘጋጅቶ እንዲቀርብ ያደርጋል፣ አፈጻጸሙን ይገመግማል፣
 • የሥራ ዘርፉን በአስፈላጊ ግብአቶች እንዲሟሉ ያደርጋል፣ ምቹ የሥራ ሁኔታዎችን እንዲፈጥሩ ያደርጋል፣
 • በሥሩ ያሉ ሰራተኞችን ይመራል፣ ይቆጣጠራል፣
 • የሠራተኞችን የሥራ አፈጻጸም ይገመግማል፣ ውጤታማ የሆኑ ሰራተኞችን ያበረታታል፣ የአቅም ክፍተት ያለባቸውን ሰራተኞች በመለየት ልዩ ድጋፍ እንዲያገኙ ያደርጋል፣
 • ወቅታዊ የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርቶችን ትክክለኛነት በማረጋገጥ ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፣
 • የተቋሙ የሥራ ድርሻ የሥርዓተ ጾታ እኩልነትን ከማረጋገጥና የሴቶችን ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ከማሳደግ አንጻር ከተቋሙ አልፎ ወደ ሌሎች የሚዘለቅ ተልዕኮ ያለው እና በተቋሙ የሚከናወኑ ተግባራት በሥርዓተ ጾታ እኩልነት ላይ የሚሳድሩት ተፅዕኖ ከፍተኛ በሆነ መ/ቤት ውስጥ የዳይሬክቶሬቱን ሥራ በመምራትና በማስተባበር የሴቶችን አቅም በመገንባት ሚናቸውን በማሳድግ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማስቻል ነው፣
 • የስራ ክፍሉን የሩብ ዓመት፣ ግማሽ ዓመትና የዓመት እቅድ ያዘጋጃል፣ ሲጸድቅም በስራ ላይ እንዲውል ያደርጋል፣
 • የስራ ክፍሉን እቅድ ማስፈጸሚያ በጀት በማዘጋጀትና በማስፈቀድ በስራ ላይ እንዲውል ያደርጋል፣
 • የስራ ክፍሉን ባለሙዎች የየእለት ስራ ይመራል፣ ያስተባብራል፣ ይገመግማል፣
 • የስራ ክፍሉን ሥራ ከሌሎች የሥራ ክፍሎች ጋር በቅንጅት እንዲሠራ ያስተባብራል፣
 • የስራ ክፍሉን ባለሙዎች የሥራ አፈፃፀም ይገመግማል፣ ግብረ መልስ ይሰጣል፣ የማብቃት ሥራ ያከናውናል፣
 • የስራ ክፍሉን ባለሙዎች ኃላፊነታቸውን በብቃት እንዲወጡ አቅማቸው የሚጎለብትበትን ሁኔታ ያመቻቻል፣ በተግባር ላይ እንዲውል ያደርጋል፣
 • በዘርፉ የወጡ ፖሊሲዎች፣ ደንቦችና መመሪያዎችን ከሥርዓተ ፆታ አንፃር እንዲቃኙ ያደርጋል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፣አተረጓጐሙም ላይ ኃላፊውን ያማክራል፣
 • ከሥርዓተ ፆታ አኳያ ሃገሪቷ ተቀብላ ያፀደቀቻቸውን ድንጋጌዎች የድርጊት መርሃ ግብር በመንደፍ ከዘርፉ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር በማጣጣም ተግባራዊ እንዲሆን ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፣
 • በዘርፉ ሥራዎች የሥርዓተ ፆታ ጉዳዮች እንዲካተቱ የአሰራር ስርዓት ይዘረጋል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ ክፍተቶችን ይለያል፣ ተገቢውን ግብረ መልስ ይሰጣል፣
 • በዘርፉ ተግባራዊ የሚሆኑ ኘሮግራሞች/ኘሮጀክቶች እንደአግባብነታቸው ሥርዓተ ፆታ ተኮር መሆናቸውን በመከታተል ተገቢውን የቴክኒክ ድጋፍ ይሰጣል ፣
 • የተቋም ባህል ለሥርዓተ ፆታ ምላሽ ሰጪ መሆኑን ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፣
 • ፕሮጀክት ይቀርጻል ፈንድ ያፈላልጋል፣
 • በዘርፉ ደረጃ ሴቶች ያሉበትን ተሣትፎና ተጠቃሚነት የሚያሳይ የተተነተነ መረጃ እንዲወጣ ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፣ ያሰራጫል፣
 • የሥልጠና ፍላጎት ዳሰሳ ጥናት እንዲካሔድ ያደርጋል፣በውጤቱ መሰረት መሠረት የአጭርና የረጅም ጊዜ ሥልጠና በአመታዊ እቅድ ውስጥ እንዲካተት በማድረግ ተፈጻሚነቱን ይከታተላል፣ልዩ ልዩ ስልጠናዎችና ቴክኒካዊ ድጋፎች የሚገኝበትን ስልትና ዘዴ ይቀይሳል፣
 • በዘርፉ በስርዓተ ፆታ ላይ ከሚሰሩ ማህበራትና አደረጃጀቶች ጋር የጋራ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የምክክር መድረክ ያመቻቻል፣ መልካም ተሞክሮዎችን ይቀምራል፣ ቅንጅት በመፍጠር ይሰራል፣
 • መንግሥታዊና መንግሥታዊ ካልሆኑ አካላት ጋር በተመሰረተ ፎረም በአቅም ግንባታ ሥራዎች ተሞክሮ በመለዋወጥ ጥሩ ሥራዎችን ያስፋፋል፣
 • የአካል ጉዳተኞችን ጉዳይ በልዩ ትኩረት ተጠቃሚነታቸው በእያንዳንዱ የስራ ዘርፍና ዳይሬክቶሬት መካተቱን ይከታትላል፤
 • የሴቶችን ሚናና መብት የሚያሳድጉ ሴሚናሮችንና ወርክሾፖችን ያዘጋጃል፣ ሴቶችን የሚመለከቱ ጥናታዊ ጽሑፎች እንዲቀርቡ ያደርጋል፡፡
 • የህግ አገልግሎቱን ሥራዎች ያቅዳል፣ ያደራጃል፣ ይመራል፣ ያስተባብራል፣
 • የሥራ ዘርፉን አፈጻጸም ውጤታማነት ይገመግማል፣ ደንቦችና መመሪያዎች በሥራ ላይ መዋላቸውንና መከበራቸውን ያረጋግጣል፣
 • የዘርፉንኧአጠቃላይ የዕቅድ አፈጻጸም ወቅታዊ ሪፖርት ለበላይ ኃላፊ ያቀርባል፤
 • መሥሪያ ቤቱን በሚመለከቱ ፖሊሲ፣ አዋጅ፣ ደንቦችና መመሪያዎች ላይ በጥናት የተደገፉ የማሻሻያ ሃሳቦችን ያመነጫል፣ እንዲመነጩ ያደርጋል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፤
 • በመሥሪያ ቤቱ የሚወጡ አዋጆች፣ ደንቦችና መመሪያዎች እና የሚፈጸሙ ስምምነቶች ከሀገሪቱ ሕጎች ጋር የማይጋጩ መሆኑን ያረጋግጣል፤
 • በመሥሪያ ቤቱየሚካሄዱ የአዳዲስና የማሻሻያ ህጎች እና የስምምነት ሠነዶች ረቂቅ ዝግጅት  ሥራዎችን በበላይነት  ይመራል፣ ውስብስብ የሆኑ ጉዳዮችን ረቂቅ በመሠሪያ ቤቱ የተዘጋጁ አዳዲስና የማሻሻያ ረቂቅ የህግ ሠነዶች በየደረጃው በውይይት ዳብረው ለሚመለከተው አካል ቀርበው እንዲጸድቁ ያደርጋል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፤
 • የመሥሪያ ቤቱን የህግ አገልግሎት ሥራዎች አፈጻጸም ለማሻሻል የሚያስችሉ ምርጥ ተሞክሮዎች የሚገኝበትን ሁኔታ ያመቻቻል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፤
 • መሥሪያ ቤቱን የሚመለከቱ ሕጐች፣ የውል ስምምነቶችና ሌሎች ህግ ነክ ሠነዶችን መተርጎም ሲያስፈልግ ሥራውን ተከታትሎ ያስፈጽማል፤
 • መሥሪያ ቤቱ ከሌላ ወገን ጋር የሚያደርጋቸው ድርድሮችና ስምምነቶች የሀገርን ጥቅም የሚያስጠብቁና ውጤታማ እንዲሆኑ የህግ ድጋፍ ይሰጣል፤
 • የሚዘጋጁ የድርድር ነጥቦችና የስምምነት ሠነዶች ትክክለኛነት ያረጋግጣል፣ የስምምነቱን አፈጻጸም ይከታተላል፣ አለመግባባቶች ሲኖሩ በሕግ መሠረት እንዲፈቱ ያደርጋል፤
 • መሥሪያ ቤቱን ወክሎ ከሌሎች መሥሪያ ቤቶችና ድርጅቶች ጋር ይደራደራል፣ ይወያያል፤
 • መሥሪያ ቤቱን የሚመለከቱ የፍርድ ቤት ክርክር ጉዳዮች የህግን አግባብ ተከትለው ተገቢውን ውሳኔ እንዲያገኙ ይከታተላል፣ ያስፈጽማል፤
 • ውስብስብ በሆኑ ጉዳዮች ላይ በፍርድ ቤቱ ክስ ይመሰርታል፣ መሥሪያ ቤቱ ሲከሰስም ይከላከላል፣
 • መሥሪያ ቤቱን በሚመለከት በሚነሱ የህግ ጉዳዮችና ጥያቄዎች ላይ ተገቢውን ማብራሪያና ምላሽ ይሰጣል፤
 • መሥሪያ ቤቱን በሚመለከቱ ህግ ጉዳዮች ላይ  የውይይትና የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች እንዲዘጋጁ ያደርጋል፣ ሥራውን በበላይነት ይመራል፤
 • ለመሥሪያ ቤቱ የበላይ አመራሮችና ለየሥራ ዘርፎች በህግ ነክ ጉዳዮች ላይ የምክር አገልግሎት ይሰጣል፤