የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለጤናችን በሚል የቢሮው አመራሮችና ሠራተኞች በስራ ገበታ ላይ እያሉ ጤናችውን ለመጠበቅ እንዲያስችል የአካል ብቃት ስፓርታዊ እንቅስቃሴ በቢሮው ቅጥር ግቢ አካሄዱ ፡፡
ይህ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በስራ መሀከል ሰውነትን ለማፍታታት እና አእምሮን ለማነቃቃት ሲሆን ሁሉም የመስሪያ ቤቱ ሰራተኞች ተሳታፊ እንዲሆኑ በማድረግም ተካሂዷል።
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ሰውነት የጭንቀት እና ድብርት ስሜትን ለማስወገድ የሚረዳውን ሆርሞን እንዲያመነጭ በማድረግ የደስተኝነት ስሜት እና ቀና አስተሳሰብ እንዲኖር ያላብሳል።