በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ የሚመራው የካፒታል ፕሮጀክቶች ክትትል ኮሚቴ ዘንድሮ በክልላችን ከግንቦት 27/2016 ጀምሮ ለሚከበረው የሀረር ቀን በዓል ጋር በተያያዘ መልካም ገጽታን ለመገንባት ፤ የኢንቨስትመንትና የቱሪዝም መስህቦችን ለማስተዋወቅ የሚረዱ ፕሮጀክቶች አፈጻጸም በሚመለከት የፕሮጀክቱ ባለቤት ተቋማት አመራሮች በተገኙበት ግምገማ አካሂዷል፡፡
በመሰረታዊ አገልግሎቶች ማለትም በትምህርት፣ ፣ በንጹህ መጠጥ ውሃ፣ በግብርናና መንገድ ዘርፎችና እንዲሁም በባህል ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ በኩል የኢኮ ፓርክ ስራዎች በተመለከተ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች አፈጻጸምና በአፈጻጸም ሂደት ተግዳሮት ሊሆኑ የሚችሉ የግዥ መጓተት፣ ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ፣ ከባለድርሻ አካለት ጋር ያለው ቅንጅታዊ ስራ ክፍተት እንደ ምክንያት ቀርቧል።
በግምገማው ወቅት የየተቋማቱ እስከ ግንቦት 30 ድረስ የሚጠናቀቁ ፕሮጀክቶችን ለይተው ቀርቦ የተገመገመ ሲሆን የካፒታል ፕሮጀክቶች ክትትል ኮሚቴ አባላትም መስተካከል ያለባቸው ጉዳዮች ላይ ገንቢ አስተያየቶች ሰጥተዋል፡፡
የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ሃላፊ አቶ መሐመድ ያህያ በበኩላቸው ተቋማቱ የበለጠ ውጤት የሚያስመዘግቡበትን ስልት ተግባራዊ ማድረግ እንዳለባቸው ጠቁመው በቀጣይ የፕሮጀክቱ ባለቤት መስሪያ ቤቶች እስከ ግንቦት 30 ድረስ የካፒታል ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ በሚያወጡት የጊዜ መርሃ ግብር መሰረት የካፒታል ፕሮጀክቶች ክትትል ኮሚቴ አባላት አስፈላጊው ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርጉ አቅጣጫ በመስጠት ስብሰባው ተጠናቋል።