የሀረሪ ክልል ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ የ2015 በጀት አመት እቅድ አፈፃፀምና የ2016 በጀት ዓመት እቅድ ግምገማ አካሄዷል ፡፡፡
የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ም/ሃላፊ የሆኑት አቶ አብዱልባሲጥ አቡበከር በግምገማ መድረክ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን የመድረክ አላማ በ2015 በጀት አመት ላይ ያጋጠሙ ችግሮችን በመለየት በ2016 በጀት አመት ችግሮችን እንዳይደገሙ በመመካከር የጋራ አቅጣጫ ለማስቀመጥ መሆኑን ገልፀዋል።
ተቋሙ በፋይናንስ ስራዎች ላይ የሚስተዋሉ የሂሳብ ጉድለቶችን በዘለቄታዊ መንገድ ለመፍታት የተለያዩ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በመጠቀም አበረታች ስራዎች ተሰርተዋል ብለዋል።
ወጪ ቆጣቢ የሆነ የበጀት ስርአትን በመከተልና ብክነትን በመቀነስ የሚመደበው በጀት ለታለመለት አላማ እንዲውል ከማድረግ አንፃር የተለያዩ መመሪያና ደንቦችን በማዘጋጀት የህግ ማእቀፎችን ጥራት ያለውና የተሻለ የማድረግ ስራ ማድረግ መቻሉንም ገልጸዋል ።
በመንግስት ፋይናንስ ላይ የበጀት አስተዳደር ስርአትን በመፍጠር ውጤታማና የተሻለ ስራ በቀጣይ በጀት ዓመትም እንደሚሰራም ተናግረዋል።
በ2016 በጀት ዓመት የሃብት አመዳደብ ውጤታማነትና የወጪ በጀት አጠቃቀምን ማሳደግ፣የመንግስት ፕሮጀክቶች አፈፃፀም፣ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ፕሮጀክት ክትትልና ድጋፍ፣ የኦዲት ሪፖርት ሽፋን ማሳደግ፣ ግልፅና ከብክነት የፀዳ ግዢና ንብረት ማስተናገድ ስርዓትና ማጎልበት በዕቅዱ የተካተቱ ዋና ግቦች መሆናቸውን አመላክተዋል፡፡
በመጨረሻም በቢሮው ለብዙ አመት ያገለገሉና ጡረታ የወጡ
ሰራተኞችን በክብር የሸኘ ሲሆን የ2015 በጀት ዓመት የአፈፃፀም ምዘና መሰረት በማድረግ የላቀ አፈጻጸም ላላቸው ሰራተኞች የእውቅና እና የምስጋና ፕሮግራም ተካሂዷል።