ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በአለም አቀፍ ደረጃ ለ111ኛ ጊዜ በአገራችን ደግሞ ለ46ኛ ጊዜ በመከበር ላይ ይገኛል፡፡ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን “ማርች 8” ሴቶች በማህበረሰቡ ውሰጥ ተገቢውን ስፍራ እንዲያገኙ መሰረት የጣለ ነው፡፡ የዓለማችን ሴቶች ባደረጉት ተጋድሎ በሴቶች ላይ ይደርሱ የነበሩ ጫናዎች ቀንሰው የእኩል ተጠቃሚነት አጀንዳ በመንግስታት ፖሊሲ ውስጥ እንዲካተት ሆኗል፡፡የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱልሃኪም አብዲ ሴቶች በርትተው በሁሉም መስክ ከሰሩ ስኬታማነታቸው የላቀ መሆኑን ገልጸው ያሰቡትን አላማ ለማሳካት ከወዲሁ መበርታት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ ለዚህም የሴቶች ሁሉን አቀፍ ተሳትፎ ሊጎለብት እንደሚገባ አሳስበዋል፡በአገራችን የፆታ እኩልነትን በማስፈን ሴቶች ከነበረባቸው ድርብርብ ተጽዕኖ ተላቀው በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ መስኮች ተሳታፊ እና ተጠቃሚ እንዲሆን ተጨባጭ እርምጃዎች ሲወሰዱ ቆይተዋል፡፡ በዚህም በርካታ ቁጥር ያላቸው ሴቶች ከራሳቸው አልፈው ለማህበረሰቡ እና ለአገር የሚጠቅሙ አኩሪ ተግባራትን ፈጽመዋል፡፡የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ከፍ በሚያደርጉ የስራ መስኮች ላይ በመሰማራት እና ሴቶችን በማሳተፍና ተጠቃሚ በማድረግ በስራቸው አንቱታን ያተረፉ የአገራችን ሴቶች ቁጥር እየጨመረ መጥቷል፡፡ በፖለቲካ መስክም በውሳኔ ሰጭነት ቀሪ ስራዎች እንደተጠበቁ ሆኖ የአገራችን ሴቶች ከፊት እየመሩ ይገኛሉ፡፡ የአለም አቀፍ የሴቶች ቀንን ስናከብርም ይሄንን የተገኘውን ድል ወደላቀ ደረጃ ለማሳደግ በመትጋት እና ሴቶች እርስ በእርስ ያላቸውን ትስስር እና ትብብር ወደላቀ ደረጃ ለማድረስ ቃል በመግባት ሊሆን ይገባል፡፡ የዘንድሮው አለም አቀፍ የሴቶች ቀንን በአገራችን ስናከበር ሴቶች አገራችን ከውስጥም ከውጭም ተወጥራ ባለችበት አስቸጋሪ ወቅት ውስጥ የአገር አለኝታ መሆናቸውን በተግባር ያሳዩበትን ተጋድሎ እያሰብን ሊሆን ይገባል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡+71,760People reached239EngagementsBoost post
17172 SharesLikeCommentShare