ከክልል ፓርቲ ጽ/ቤት፣ ከፕሬዝዳንት ጽ/ቤትና ከፕላንና ልማት ኮሚሽን የተውጣጡ ቡድኖች የቢሮውን የአጋማሽ አመት ዕቅድ አፈፃፀምን በተጨባጭ ከተከናወኑ ስራዎች አንፃር በጥልቀት የመገምገም ስራ ተከናውኗል ።
በግምገማው የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር ስራን ዘመኑ በሚጠይቀው ቴክኖሎጂ ከማዘመን አንጻር የተሰሩ ስራዎች፣ቅንጅታዊ አሰራር ፣የኦዲት ጉድለት ላይ የእርምት እርምጃዎች የማስወሰድና የበጀት አያያዝና አጠቃቀምና ተያያዥ ጉዳዮች አኳያ የተከናወኑ ስራዎችን ገምግመዋል።
የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ኃላፊ አቶ መሀመድ ያህያ መመሪያዎችን ከማሻሻል ፣ በጀትን በፍትሃዊነት ከመደልደል፣ የአዲት ግኝት በተመለከተ እርምጃ እንዲወሰድ ከማድረግ አኳያ ከመንግስት ግዥና ንብረት አያያዝ ጋር በተገናኘ ቢሮው ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ለቡድኑ አብራርተዋል።
የመንግስትን ሃብት እና በጀት በአግባቡ ለታለመለት አላማ እንዲውል ለማድረግ የተሰሩ ስራዎች በተመለከተ ገለፃ አድርገዋል ።
የገምጋሚ ቡድኑ ቢሮው የፋይናንስ ግልፀኝነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት እና ቀልጣፋ የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓትን በመዘርጋት የተገልጋዩን እርካታ ለማሳደግ የተሰሩ ስራዎችን ተመልክቷል፡
መረጃዎችን ለዜጎች ተደራሽ ከማድረግ ፣የሴቶች ተሳትፎ ከማሳደግ አንጻር የተከናወኑ ስራዎች ተብራርቷል።
በአፈጻጸም ረገድ ስላጋጠሙ ችግሮችና ቀጣይ አቅጣጫዎች ሰፋ ያለ ማብራሪያዎች ሃሳቦች ተነስተዋል።
የአገልግሎት አሰጣጥ አፈፃፀም ምዘና ዋንኛ አላማ ተቋሟት ያሉበትን ደረጃ ለመለየት እና በቀጣይ ለሚኖረው የስራ ጊዜ ያሉባቸውን ክፍተቶች በመለየት መሙላት እንደሆነ ተገልጿል ።