የሀረሪ ክልል ምክር ቤት ለ2017 የበጀት አመት የክልሉ በጀት ከ5 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ አፀደቀ።
የሀረሪ ክልል ምክር ቤት ባካሄደው 6ዙር 3ኛ አመት 6ኛ መደበኛ ጉባኤ የክልሉ መንግሥት የ2017 በጀት ከ5 ቢሊየን 203 ሚሊየን ብር በላይ አጽድቋል።
የክልሉ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ኃላፊ አቶ መሀመድ ያህያ ከተያዘው በጀት 56 በመቶ ለካፒታል በጀት እንዲሁም 42 በመቶው ደግሞ ለመደበኛ በጀት የሚውል ነው ብለዋል።
በጀቱም በዋናነት በክልሉ ከተለያዩ ገቢዎች ከሚሰበሰብ ገቢ እና ከፌዴራል መንግስት ድጎማ የሚሸፈን መሆኑን ተናግረዋል።
በጀቱ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ22 በመቶ ብልጫ እንዳለው ገልጸዋል።
የክልሉ ምክር ቤትም በጀቱ ለታለመለት አላማ እንዲውል አቅጣጫ አስቀምጧል።