የወረዳው የ2013 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀምና የ2014 በጀት ዓመት አቅድ በማስመልከት ለባለድርሻ አካላት ውይይት ተደርጓል።በመድረኩ የፋይናንስ ግልጸኝነትና ተጠያቂነት እንዲሁም የ2013 በጀት ዓመት አፈፃፀም ግምገማ እና የ2014 በጀት ዓመት እቅድን በማስመልከት የተዘጋጀ ሰነድ ለተሳታፊዎች ገለጻ ቀርቦዋል። የፋይናንስ ግልጸኝነት እና አሰራር ለባለ ድርሻ አካላት በግልፀኝነት እንዲሰሩ በማድረግ የሀብት ብክነትን ለመከላከል በትኩረት መስራት እንደሚያስፈልግ የሸንኮር ወረዳ መስተዳደር አስተዳዳሪ አቶ ኻሊድ አብዲ ተናግረዋል።
ውስን የሆነውን በጀት ፍትሃዊ በሆነ መንገድ መጠቀምና በስራ ላይ ስለመዋሉ የሚገነዘብ ህብረተሰብ መፍጠርና በግዥ ስርዓቱ ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን ማረም የመንግስት ብቻ ሳይሆን የሁሉም ባለ ድርሻ አካላት ሀላፊነትም ጭምር በመሆኑ በቀጣይ ተቀዳሚ ተግባር ተደርጎ መሰራት እንዳለበት ተሳታፊዎች አሳስበዋል።
በየደረጃው ያለው የፋይናንስ አንቀሳቃሽ አካላት በተግባሩ ጥልቅ ግንዛቤ እንድኖራቸው ማድረግ ለህብረተሰቡ ተጠቃሚነት ሚናው ከፍተኛ መሆኑና በፋይናንስ አስተዳደር መመሪያና ህገ ደንብመሰረት መስራት የመልካም አስተዳደር ችግርን ይቀርፋል፨
በተጨማሪም ከዚህ በፊት የታዩትን ክፍተቶች በማሻሻል በቀጣይ የስራ ዘመን የተሻለ ስራ ለመስራት የሚረዳ በመሆኑ ለወረዳው ህብረተሰብ በፋይናንስ ግልፀኝነትና አሰራር ግንዛቤ በመፍጠር የሀብት ብክነትን ለመከላከለ እንሰራለን ብለዋል፡፡