የሀረሪ ክልል ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ በማህበራዊ ተጠያቂነት ፕሮግራም ትግበራ ዙሪያ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሂዷል ። ማህበራዊ ተጠያቂነት ዜጎች በማንኛውም ደረጃ በሚገኝ የመንግስት አገልግሎት ተሳትፎ የሚያደርጉበት ሂደት ሲሆን በተሳትፎውም የመንግስት አገልግሎት ግልፅ፣ ተጠያቂነት ያለበት፣ ውጤታማ የሆነ፣መልካም አስተዳደርን በማስፈን የመንግስት አስተዳደር እንዲሻሻል እንደሚያደርግ እና በተጨማሪም የአንድ አገር ዜጎች መብታቸውንና ግዴታቸውን በውል እንዲረዱ በማድረግ ንቁና ነፃ የሆነ ዲሞክራሲያዊ ማህበረሰብ መፍጠር እንደሚያስችልም በመድረኩ ተገልጿል ።በአጠቃላይ ማህበራዊ ተጠያቂነት የመንግስት አገልግሎት ከሙስና የፀዳና ውጤታማ እንዲሆን በማስቻል በአንድ አገር ውስጥ ሁለንተናዊ ልማት እንዲረጋገጥ ማድረግ ነው ተብሏል ፡፡