የተቋሙ አፈፃፀም ሪፖርት በዕቅድና ዝግጅት ግምገማ ዳይሬክቶሬት የ2015 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም በበጀት ዓመቱ ታቅደው የተከናወኑ ቁልፍና አበይት ተግባራት ግቦችና አፈፃፀም ሪፖርትና እያንዳንዱ ዳይሬክቶሬት የየክፍሉን የ2016 በጀት አመት እቅድ አቅርቦ አስገምግሟል። በቀረበው የአፈፃፀም ሪፖርትና በቀጣይ በ2016 በጀት አመት ከበጀት አስተዳደር፣ ከመንግስት ፋይናንስ፣ ከውስጥ ኦዲት፣ ከግዥ ፣በቻናል አንድ የሚተገበሩ ፕሮግራሞችና ሌሎች ስራዎችም አፈጻጸምና ሊሰሩ የታቀዱ ስራዎች ቀርቦ በገንዘብና ኢኮሚ ትብብር ቢሮ ሃላፊ አቶ መሐመድ ያህያ መሪነት ሰፊ ውይይት ተካሂዶባቸዋል፡፡ ከተከናወኑ በርካታ ተግባራት መካከል በጥንካሬ ትምህርት የሚወሰድባቸውን በመለየት የማስፋት እና ቀጣይነቱን የማረጋገጥ ሂደት ላይ በትኩረት ውይይት ተደርጓል፡፡
እንዲሁም ባለፈው በጀት ዓመት የነበሩ እጥረቶችን እና ጉድለቶችን በመለየት የመሙላትና የእርምት እርምጃ መውሰድ የሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይም በስፋት ተወያይቷል፡፡
በተጨማሪም በቀጣይ በጀት ዓመት ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት በመፍጠር ቢሮው ለሁለት ተከታተይ ቀናት ሲያካሂደው የነበረውን የ2015 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸምና የ2016 በጀት ዓመት እቅድ ግምገማ በዛሬው እለት አጠናቋል፡