




የመሰረታዊ አገልግሎቶች አቅርቦትና የማህበራዊ ተጠያቂነትፕሮግራሞች የጋራ የውይይት መድረክ ተካሄደ።
ዜጎች መሰረታዊ አገልግሎቶችን በፍትሃዊነትና በጥራት ማግኘት እንዲችሉ መንግስት ከተባባሪ አጋሮች ጋር በመሆን ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እየሰራ ነው።
በሀረሪ ክልል የህብረተሰቡ የመሰረታዊ አገልግሎት ተደራሽነት እንዲሰፋና ሁሉን አቀፍ የማህበራዊ እድገት እንዲኖራቸው ለማስቻል ከአለም ባንክ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ፕሮግራም ተቀርጾ በመተግበር ላይ ይገኛል።
በፕሮግራሙ አፈፃፀም ዙሪያ በተደረገው የውይይት መድረክ ላይ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትበብር ቢሮ ሃላፊ አቶ መሐመድ ያህያ እንዳሉት መንግስት በአለም አቀፍ ከልማት ማህበር ጋር በመተባበር የሚተገበራቸውን የመሰረታዊ አገልግሎቶችና የማህበራዊ ተጠያቂነት ፕሮግራሞችን የአፈፃፀም ደረጃ ለፕሮግራሞቹ በተቀመጡት ውጤት አመላካች መለኪያዎች አማካይነት ለመለካት ይረዳ ዘንድ በየግማሽ ዓመቱ የጋራ የውይይት መድረክ ቢሮው እንደሚያዘጋጅ ገልጸዋል ።
ማህበራዊ ተጠያቂነት ማንም ኃላፊ ለሆነበት ነገር ተጠያቂ እንደሆነና ማንኛውም አካል አገልግሎት በሚሰጥበት ወቅት ከህብረተሰቡ ፍላጎት ጋር እንዲጣጣም በማድረግ በተለይም በመሰረታዊ የአገልግሎት ዘርፎች ማለትም በውሃ፣ በጤና፣ በትምህርት፣ በግብርና ዘርፎችና በሌሎች የስራ ዘረፎች ላይ የህብረተሰቡ ፍላጎቶች እና ስራዎች ስለመጣጣማቸው ቁልፍ በአገልግሎት መለኪያ ደረጃዎች መሰረት ስለመሆናቸው በየጊዜው ውይይቶች በማድረግ የማስተካከያ ሃሳቦች የሚወሰድበት እንደሆነ ተናግረዋል ።
በዜጎችና የህዝብ አገልጋዮች መካከል ገንቢ የሆኑ የሀሳብ ልውውጥ በማዳበር የአገልግሎቶችን እንዲገመግሙና እንዲያሻሽሉ የሚያስችል በመሆኑ ጠቀሜታው የጎላ ነው፡ ብለዋል።፡
ተቋማቱ ውጤታማ እንዲሆኑ ለማድረግም የህዝብ ተሳትፎን ከማጠናከር ይጠበቅብናል ብለዋል።
አፈፃፀሙን በሚመለከት ከጤና፣ ትምህርት ፣ንፁህ መጠጥ ውሃ አካባቢና በሌሎች ዘርፎች ሪፖርቶች ቀረቦ ውይይት ተደርጎበታል ።
በመጨረሻም የቀረበው ሪፖርት በተመለከተ ከቤቱ የተነሱ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ላይ የማጠቃለያ ሀሳብ የሰጡት የገንዘብና ኢኮኖሚ ትበብር ቢሮ ሃላፊ አቶ መሐመድ ያህያ የተሻለ የጋራ ውጤት ለማምጣት እንዲያስችል ቢሮው አስፈላጊውን ድጋፍና እገዛ እንደሚያደርግ በመግለፅ መድረኩ ተጠናቋል።






